1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሬቻ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ

ቅዳሜ፣ መስከረም 24 2012

ኢሬቻ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ለግምት የሚያስቸግር በርካታ ህዝብ በተገኘበት ተከብሯል። ከማለዳው ጀምሮ ለዚሁ ክብረ በዓል  ሲባል በተዘጋጀው አነስተኛ የተከተረ ውሃ ወይም ሆራ ፊንፊኔ በአባ ገዳዎች ምርቃትና የደስታ መልዕክት ተጀምሮ በድምቀት ሲከበር ነዉ የዋለዉ።

Äthiopien Irrecha Feierlichkeiten in Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

በዓሉ በደስታ ተከብሮአል

This browser does not support the audio element.

የኢሬቻ በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ ለግምት የሚያስቸግር በርካታ ህዝብ በተገኘበት ተከብሯል። ከማለዳው ጀምሮ ለዚሁ ክብረ በዓል  ሲባል በተዘጋጀው አነስተኛ የተከተረ ውሃ ወይም ሆራ ፊንፊኔ በአባ ገዳዎች ምርቃትና የደስታ መልዕክት ተጀምሮ በድምቀት ሲከበር ነዉ የዋለዉ። ከተለያየ የኦሮሚያ አካባቢ የተሰባሰበ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የበዓሉ እድምተኛ  ልዩ ልዩ የኦሮሞ ባህላዊ አልባሳትን በመልበስ፣ ኅብረት ዝማሬዎችን በማሰማትና በመጨፈር ስርዓተ በዓሉን በደስታ አክብሯል። በዚሁ በዓል ላይ የተለያዩ ብሔረሰብ ተወካዮችም በመታደም የሥነ ስርአቱ ድምቀት ሆነዋል። በአዲስ አበባ የኢሬቻ በዓል አከባበር በአማረ መልኩ መጠናቀቁ ተመለከተ። የከተማዉ አስተዳደር በአከባበሩ ላይ ሁሉ ለተሳተፉና ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ምስጋናን አቅርቦአል። ትናንት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደዉ የኢሩቻ በዓል ዝግጅት ሥነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁንም የከተማዉ ፖሊስ መሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል። በነገዉ እለትም  ኢሬቻ በሆራ ቢሾፍቶ ይከበራል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW