1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኢሮብ ሕዝብ ተቃዉሞ

ዓርብ፣ ሰኔ 1 2010

ዛሬ ደሐን በተባለች ከተማ የተሰለፉት የኢሮብ ብሔረሰብ አባላት እንደሚሉት ግን ዉሳኔዉ የኢሮብን ሕዝብ ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ አይቀበሉትም

Äthiopien Proteste gegen die EEBC-Entscheidung
ምስል DW/A. Desta

 

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ፤ የኢትዮጵያ ኤርትራን የድንበር ዉዝግብ ያስወግዳል ተብሎ የነበረዉን ሥምምነት እና ዉሳኔን ገቢር እንደሚያደርግ ማስታወቁን የምሥራቅ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች ተቃወሙት።የኢሕአዴግ ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈዉ ማክሰኞ ባሣለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ኢትዮጵያ የኢትዮ-ኤርትራን የሠላም ዉል እና የድንበር አካላይ ኮሚሽኑን ዉሳኔ ገቢር ታደርጋለች። ዛሬ ደሐን በተባለች ከተማ የተሰለፉት የኢሮብ ብሔረሰብ አባላት እንደሚሉት ግን ዉሳኔዉ የኢሮብን ሕዝብ ለሁለት የሚከፍል በመሆኑ አይቀበሉትም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለስ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW