1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሰመኮ መግለጫ ስለኢትዮጵያ

ሰለሞን ሙጬ
ረቡዕ፣ መስከረም 15 2017

በኢትዮጵያ የግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አምስት ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐሳወቀ ። ኢሰመኮ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እሥራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እሳሳቢ መሆናቸውን ጠቅሷል ።

Äthiopien Menschenrechtskommission
ምስል Solomon Muche/DW

የኢሰመኮ የመብት ጥሰቶች የምርመራ ውጤት

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ የግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አምስት ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐሳወቀ ። ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. መጀመሪያ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን የምርመራ ውጤት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ እንዳለው፣ «ከሕግ ውጭ የሚፈጸም ግድያ፣  በግጭት ዐውድና አካባቢ የሚደርስ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ» መቀጠሉን ዘርዝሯል ። ኢሰመኮ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እሥራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እሳሳቢ መሆናቸውን በመግለጫው ጠቅሷል ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶች የምርመራ ውጤት

በኢትዮጵያ የግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አምስት ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። ኮሚሽኑ ከሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2017 ዓ.ም. መጀመሪያ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን የምርመራ ውጤት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ እንዳለው፣ ከሕግ ውጭ የሚፈጸም ግድያ፣ በግጭት ዐውድና አካባቢ የሚደርስ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ" መቀጠሉን ዘርዝሯል።

ኢሰመኮ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እሥራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እሳሳቢ መሆናቸውን በመግለጫው ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የመብት ጥሰቶች የምርመራ ውጤት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ተፈፀሙ ያላቸውን ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ በእለት እና ቀን ዘርዝሮ አውጥቷል። የምርመራ ግኝት ውጤቱ ግድያዎች የተፈፀሙት አንድም በታጣቂ ቡድኖች በሌላ በኩል በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት እና በታጣቂዎች በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ እንዲሁም  በመንግሥት የፀጥታ አካላት መሆኑን ያሳያል።

በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ሸኔ እንዲሁም በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች የጥፋት ተሳትፎ እና በእነዚህ ታጣቂዎች ላይ የደረሰው ጉዳትም ውጤቱ ኮሚሽኑ በጠቀሳቸው ጥፋት የተፈፀመባቸው እለታት በዝርዝር ተጠቅሷል። የኢሰመኮ መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለጉብኝት እና ለፊልም ሥራ ከተንቀሳቀሱ ሰዎች መካከል 1 የስፔን ዜግነት ያለው ሰው በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል ሲል ይጠቅሳል።

ማንነት ተኮር ተደጋጋሚ ጥቃት እና ግድያ ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች አንዱ

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል ጆር ወረዳ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ. ም በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት 47 ሰዎች ሲገደሉ ጥቃቱ በደረሰበት በዚሁ ቀን ቢያንስ 700 የሣር መኖሪያ ቤቶች፣ 1 የጤና ኬላ እና 2 ትምህርት ቤቶች ተቃጥለዋል ብሏል። በዚሁ ክልል ጀዊ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አካባቢ ታጠቂ ቡድኖች በተፈጸመ ጥቃት 3 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ተገድለው፣ 3 ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱም ተመላክቷል። በዚሁ ጉዳይ በኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑትን ዶክተር አለሙ ምህረቱን  ጠይቀናቸዋል። 

የኢሰመኮ የምርመራ ውጤት ምን ያሳያል?

የኢሰመኮ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው በከተሞች በተለይም በባህር ዳር የቦምብ ጥቃቶች ስለመፈፀማቸው፣ ተደንግጎ ከነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተገናኘ የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ ጅምላና የተራዘመ እሥራት እንዲሁም  የተፋጠነ ፍትሕ እጦት በስፋት እንደነበር አትቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተፈፃሚነት ጊዜ ቢያበቃም "ሸኔን እና ፋኖን ትደግፋላችሁ" የተባሉ ሰዎች ከቀናት እስከ ወራት ለእሥር መዳረጋቸውን ብሎም አሁን ድረስ ታሥረው የሚገኙ ሰዎች  መኖራቸውን አስታውቋል።

ብሔራዊው የመብት ተቋም - ኢሰመኮ በኢትዮጵያ እገታ አስከፊ ገጽታ ያለው ችግር መሆኑን፣ የሀገር ውስጥ መፈናቀል፣ የመዘዋወር ነጻነትና ትራንስፖርት ላይ የተጣሉ "ሕገወጥ" ያላቸው ገደቦች የዜጎችን ሁለንተና ፈተና ውስጥ መጣላቸውን በምርመራ ውጤቱ ለማሳየት ጥሯል።

የኢትዮጵያ ካርታ

ይህንን ዝርዝር የመብት ሁኔታ ያወጣው ኮሚሽኑ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ" ጠይቋል። አያይዞም በማናቸውም የግጭት ሂደት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎች ጥሰትን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፤ በግጭቱ የሚፈጸሙ ጥሰቶችን በይፋ እንዲያወግዙ እና ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፤ እንዲሁም በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሰብአዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ" ጠይቋል።

እነዚህ አካላት በሲቪል ሰዎች ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስም እንዲቆጠቡም ጥሪውን አቅርቧል። ኮሚሽኑ "አስገድዶ መሰወርንና ሰዎች ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየትን" በሚመለከት ራሱን የቻለ ዝርዝር መግለጫ ወደፊት ይፋ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጿል።

ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዺንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል

ስለ መርዓዊ ከተማ ግድያ የዓይን እማኝ ምስክርነት

ትግራይ ክልል ሰብአዊ ሁኔታው የከፋ ሆኖ ቀጥሏል ተባለ

አሳሳቢው የሰብአዊ መብት ጥሰት በጋሞ ዞን

 

ኢሰመኮ

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዺንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW