1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ለተፈናቃዮች የሚሰጠው ድጋፍ ከሚገኙበት እጅግ አሳሳቢ የሰብአዊ ቀውስ አንጻር በቂ አይደለም።»

ሰኞ፣ ጥቅምት 26 2016

ኢሰመኮ በመግለጫው በቂ የምግብ እርዳታ አለመቅረቡ ተፈናቃዮችን ለርሃብ በተለይም ህጻናትን ደግሞ ለመቀንጨር ዳርጎአቸዋል ብሏል።በአፋር ክልል በአጠቃላይ ከ800,000 በላይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ መረዳቱን አሳውቋል፡፡ በዚህ ክልል ከ120,000 በላይ እናቶችና ሕፃናት በምግብ እጥረት መጠቃታቸውም ተነግሯል።

 የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ስርቆት ወይም ማሸሽ ተፈጽሟል በሚል ዓለማቀፍ ተራድዖ ተቋማት ድጋፍ ማቋረጣቸው ደግሞ ችግሩን እንዳባባሰው የኮሚሽኑ የስደተኞች፣ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች መብቶች ዳይሬክተሯ  እንጉዳይ መስቀሌ ነግረውናል፡፡
ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሊ እና በጋምቤላ ክልሎችም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁኔታው ተመሳሳይ ነው ተብሏል።  ምስል Alemenw Mekonnen/DW

የኢሰመኮ አስቸኳይ ጥሪ

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው ህይወታቸው እና ሰብዓዊ መብታቸው አደጋ ውስጥ ለሚገኘው ተፈናቃዮች አደጋውን የሚመጥን አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ፡፡ኮሚሽኑ በተፈናቃዮች ዙሪያ ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ ውጤት በመግለጫ ሲያሳውቅ የሁሉም አካላት ርብርብ እና እገዛን የሚጠይቅ ነው ብሏል፡፡ ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የምግብ ድጋፍ እንዲደርስም የፌዴራል መንግሥት ሰብአዊ ድጋፍ ከሚያቀርቡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ጋር ቅንጅትና ትብብርን እንዲያጠናክርም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የቀረቡ አቤቱታዎችን መነሻ በማድረግ አከናወንኩ ባለው ከሃምሌ እስከ ተያዘው የጥቅምት ወር መደበኛ ክትትል በፌዴራል እና በክልሎች የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮዎች በኩል አቅርቦት ቢደረጉም እየተሰጠ ያለው ድጋፍ ተፈናቃዮች ካሉበት እጅግ አሳሳቢ የሰብአዊ ቀውስ አንጻር በቂ አይደለም ብሏል፡፡ የተፈናቃዮች መልሶ ማቋቋም እና ስጋቶቹ

በተለይም በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች የተወሰኑ አካባቢዎችን በአካል በመገኘትና በሌሎች የክትትል ስልቶች ምርመራ ማደረጉን ያሳወቀው ኮሚሽኑ የሚሰጡ ድጋፎች በተለይም ልዩ ድጋፍ (Special needs) የሚያስፈልጋቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያላማከለ መሆኑን መገንዘቡም አስረድቷል።በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታን አሳሳቢነት ከዚህ ቀደም በዓመታዊ ሪፖርት መቅረቡን አስታውሰው ስለዚህ መግለጫ ተጨማሪ ማብራሪያ ለዶቼ ቬሌ የሰጡት በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞች፣ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች መብቶች ዳይሬክተር  ወ/ሪት እንጉዳይ መስቀሌ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ የሚቀርብ የድጋፍ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው ብለዋል፡።

”ኢሰመኮ በመግለጫው በአፋር ክልል በአጠቃላይ ከ800,000 በላይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ ከክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር እና ምግብ ዋስትና መረዳቱን አሳውቋል፡፡ ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

“በዓመታዊ ሪፖርታችን ያልተካተቱ የምዕራብ ኦሮሚያ እና የትግራይ ተፈናቃዮች ሁኔታን በዚህ ሪፖርታችብ አጠናቅሬናል፡፡ በአማራ እና አፋር ክልሎች ያሉ የተፈናቃዮች ሁኔታንም በዚህ መግለጫችን አተኩረንበታል፡፡ በዚሁ ክትትላችን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ መሆኑንም ተረድተናል፡፡ በቂ የምግብ እርዳታ አለመቅረቡም ተፈናቃዮችን ለርሃብ በተለይም ህጻናትን ደግሞ ለመቀንጨር ዳርጎአቸዋል፡፡”ኢሰመኮ በመግለጫው በአፋር ክልል በአጠቃላይ ከ800,000 በላይ የምግብ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዳሉ ከክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር እና ምግብ ዋስትና መረዳቱን አሳውቋል፡፡ በዚህ ክልል ከ120,000 በላይ እናቶችና ሕፃናት በምግብ እጥረት መጠቃታቸውም ተነግሯል። በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተጎዱ ኪልባቲ ረሱ፣ ኢረብቲ፣ አብዓላ፣ በራሃሌ እና መጋሌ ወረዳዎች በተለይ ሰፊ የእርዳታ የቅርቦት ችግር እና የከፋ የሸቀጦች ዋጋ መናር የምግብ ዋስትናውን አሳሳቢ አድርጎታልም ነው የተባለው።በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶችት ጥሰቶች

በአማራ ክልልም  በተወሰኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያዎች የምግብ ድጋፍ ብደረግም በአብዛኛው በክልሉ ካለው የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎት አንጻር ሰፊ ችግር ስተዋላል ተብሏል፡፡ ለአብነትም ሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኘው የጃራ መጠለያ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም. የተደረገ ድጋፍ ከ4 ወራት ድጋፍ መቋረጥ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ በቅርቡ ከሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ (አውራ ጎዳና ቀበሌ) ተፈናቅለው በመልካ ጅሎ ቀበሌ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልሎ የሚገኙ ከ3,000 በላይ ተፈናቃዮች በመንግሥት በኩል የተደረገላቸው ድጋፍ የለም ተብሏልም።የጃራ ካምፕ ተፈናቃዮች እሮሮ

ኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖችም በቂ፣ ተደራሽ እና ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ እንደማይቀርብም ተነግሯል፡፡ በተለይም ሸማቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በሚዋጉባቸው አከባቢዎች በሰላም እጦት ምክኒያት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ተከስቷልም ብሏል የኢሰመኮ መግለጫ። በትግራይ ክልል ኮሚሽኑ በአካል ተገኝቶ ክትትል ባደረገባቸው አከባቢዎች ለተፈናቃዮች የመጨረሻው የምግብ ድጋፍ የቀረበው በባለፈው 2015 ዓ.ም ጥር እና መጋቢት ወራት ነው ያለው የኢሰመኮ መግለጫ፤ በክልሉ በምግብ ድጋፍ መቋረጥ ሳቢያ የሞቱና በሞት አፋፍ ያሉ በርካታ ተፈናቃዮች አሉ ብሏል፡፡ የትግራይ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራርን ዋቢ ያደረገው ኢሰመኮ በ5 ከተሞች በሚገኙት ከ53 የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎቸ በተወሰደ ናሙና ቢያንስ 1,329 ተፈናቃዮች በምግብ እጥረት ብቻ መሞታቸውን አረጋግጧል፡፡ 970 ከ5 ዓመት በታች ህጻናት ደግሞ ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፡፡

“በተለይም ከባለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ ረጂ ተቋማቱ እርዳታቸውን ማቆማቸው የምግብ አቅርቦቱን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል፡፡ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬያቸው አለመመለሳቸውና በድጋፍ የሚኖሩ መሆናቸው ደግሞ ተፈናቃዮችን እጅግ የከፋ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉን በክትትላችን አረጋግጠናል፡፡ ምስል Million Haileselassie/DW

ኢሰመኮ ክትትል ባደረገባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሊ እና በጋምቤላ ክልሎችም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ሁኔታው ተመሳሳይ ነው ተብሏል።  የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ስርቆት ወይም ማሸሽ ተፈጽሟል በሚል ዓለማቀፍ ተራድዖ ተቋማት ድጋፍ ማቋረጣቸው ደግሞ ችግሩን እንዳባባሰው የኮሚሽኑ የስደተኞች፣ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ፍልሰተኞች መብቶች ዳይሬክተሯ  እንጉዳይ መስቀሌ ነግረውናል፡፡ “በተለይም ከባለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ ረጂ ተቋማቱ እርዳታቸውን ማቆማቸው የምግብ አቅርቦቱን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል፡፡ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬያቸው አለመመለሳቸውና በድጋፍ የሚኖሩ መሆናቸው ደግሞ ተፈናቃዮችን እጅግ የከፋ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉን በክትትላችን አረጋግጠናል፡፡ ለአብነት ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ክትትል ባደረግንባቸው አከባቢዎች አርሶአደሮቹ ወይ አርሰው ለመብላት የጸጥታ ሁኔታው ስለማይፈቅድ መሰል ችግር ውስጥ ወድቀዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት የሰብዓዊ መብቶች ይዞታን እንዲያሻሽሉ ውትወታዎች እናደርጋለን ማለት ነው፡፡”እንደ የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የቅርብ ጊዜ መረጃ በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ብቻ 3.6 ሚሊየን ገደማ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW