1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሰመጉ ሃላፊ ተሰደዱ፤ በሦስቱ የሲቪክ ማኅበራት ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሰራተኞቹ በመንግሥት የፀጥታ አካላት የሚደርስባቸው ከፍተኛ ማዋከብና ጫና እንዲቆም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትን ጨምሮ ለዋና ዋና የመንግስት ተቋማት አቤት ቢልም ጫናውና ዛቻው ተባብሶ አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ የድርጅቱን ዋና ሃላፊን ጨምሮ "በርካታ ሠራተኞች ሥራቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል" ሲል አስታውቋል።

አቶ ዳን ይርጋ የኢሰመጉ ዋና ሃላፊ
አቶ ዳን ይርጋ የኢሰመጉ ዋና ሃላፊ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የኢሰመጉ ሃላፊ አቶ ዳን ይርጋ ተሰደዱ፤ በሦስት የሲቪክ ማኅበራት ላይ የተጣለው እግድ ተነሳ

This browser does not support the audio element.


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በምህጻሩ ኢሰመጉ ዋና  ሃላፊ አቶ ዳን ይርጋ የሚደርስባቸው ወከባ በመባባሱ ምክንያት አገር ለቀው መሰደዳቸውን ድርጅቱ አረጋገጠ። ሃላፊው አቶ ዳን ይርጋ  የደረሰባቸው ጫና፣ ዛቻና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ምክንያት "ለሕይወታቸው በመሥጋት" ስራቸውን ለቀው ከአገር ለመሰደድ መገደዳቸውን የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የርሳቸው ከሀገር መውጣት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸም ወከባ ሥራቸውን በነፃነት እንዳያከናውኑ እንቅፋት በመፍጠር ሀገራቸውን ትተው እንዲሰደዱ እያደረገ መሆኑ ማሳያ ነው ሲል ኢሰመጉ ጠቁሟል። ይህም የሲቪክ ምህዳርን "የሚያጠብ እና በመደራጀት መብት ላይ ጥላውን የሚጥል ነው" ሲልም አሳስቧል። በሌላ በኩል "የአገር እና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሥራት ከባድ የሕግ ጥሰት ፈጽመዋል" በሚል ታግደው የቆዩ ሦስት የሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ ዙሪያ የሚሠሩ ሲቪክ ድርጅቶች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ዕግዱ ተነስቶላቸው መደበኛ ሥራቸውን መጀመራቸውን ገልፀዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

የሲቪል ማሕበራት እና አመራሮቻቸው እየገጠማቸው ያለው ችግር

ኢሰመጉ የገጠመው ፈተና እና ችግር 


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በሰራተኞቹ ላይ በመንግሥት የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ማዋከብና ጫና እየደረሰበት መሆኑን ጠቅሶ ይህ እንዲቆም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትን ጨምሮ ለዋና ዋና የመንግሥት ተቋማት አቤት ቢልም ይልቁንም ጫናውና የሚደርስበት ዛቻ ተባብሶ አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ጨምሮ "በርካታ ሠራተኞች ሥራቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል" ሲል ገልጿል። የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ  "ብዙ ሠራተኞች ለቀውብናል። ብዙ ሠራተኞች በዚህ ሁኔታ ውስጥ መሥራት ተቸግረው ለቀዋል። እና ደግሞ የድርጅታችን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ዳን ይርጋ ከሥራው ለመልቀቅ እና ለመሰደድ ተገደዋል"። ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።የሲቪል ማኅበረሰብ ምህዳር የመዳከም ሥጋት

የኢሰመጉ አርማምስል Ethiopian Human Rights Council

በሲቪክ ድርጅቶች ላይ  የተጣለው ዕግድ ያሳደረው ዐሉታዊ ጫና

በሌላ በኩል በሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ በዴሞክራሲ ባሕል ዕድገት ላይ በሚሠሩ ሦስት ሀገር በቀል የሲቪክ ድርጅቶች ላይ በኢትትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተጥሎ የነበረው እገዳ ሰሞኑን መነሳቱን ኢሰመጎ በበጎ ተመልክቶታል። ታግደው ከነበሩ የሲቪክ ድርጅቶች መካከል አንዱ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ነው። ካርድ "የዘፈቀደ" ያለው ዕግድ ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር "ከፍተኛ እና ተደጋጋሚ ጥረቶች" ከተደረጉ በኋላ መነሳቱን ጠቅሷል። 
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ራኬብ መሰለ በኢትዮጵያ እየተደረጉ ባሉ ብሔራዊ ምክክሮች መሰል ተቋማት ሊገለሉ እንደማይገባ ሰሞኑን በተደረገ ውይይት መነጋገሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል። በቅርቡ ሦስት የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው ዕገዳ አብዛኛውን የሲቪክ ማኅበረሰብ ሥጋት ላይ እንደጣለ አንስተዋል። ኢትዮጵያዊ ተነሳሽነት ለሰብዓዊ መብቶች የተባለው ሀገር በቀል የሲቪክ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ሰለሞን በዚህ ጉዳይ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት "መንግሥት ከፈለገ ማስከበርም አለመጣስም ይቻላል።አሁን ባለንበት ሁኔታ ግን ይህንን ማድረግ የሚቸል ሆኖ አልተሰማኝም"ብለዋል።

የሲቪክ ምህዳሩ እንዳይጠብ የቀረቡ ጥሪዎች

 

ኢሰመጉ እየደረሰ ያለው መሰል ከፍተኛ ጫና "የሲቪክ ምህዳሩን የሚያጠብ፣ የታዩ መልካም ጅምሮችን የሚያቀጭጭ በመሆኑ "እነዚህ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ጠይቋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ " በሥራ ቦታችን ላይ እስከ ቢሮ መሰበር እና መዘረፍ ድረስ እየደረሱብን የነበሩ ጫናዎች ቀስ በቀስ ድርጅቱን አደጋ ውስጥ የሚከቱ ናቸው" ብለዋል። 
"አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ" የመብት ጥሰቶች

ሌላኛው ዕግድ ተጥሎበት የነበረው የሲቪክ ድርጅት የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ሲሆን "ዕገዳዉ ፈጽሞ የማይገባ የነበረ ከመሆኑም በላይ ፀንቶ በቆየባቸዉ ቀናት ከፍተኛ ጉዳት" እንደደረሰበት አስታውቋል። ሁኔታው "በአጠቃላይ የሲቪል ማህበረሰቡ የመንቀሣቀሻ ሜዳና በተለይ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የሕግ የበላይነት እና ፍትሕ እንዲሰፍን የሚደረገውን ጥረት የሚገታ በመሆኑ መንግሥት ጉዳዩን እንዲመለከተው ጠይቋል። 


ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW