1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ሕግ እና ፍትሕአፍሪቃ

የኢትዮጵዊያን ግድያ በጆሃንስበርግ

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2018

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተመተው መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና የአገሪቱ ፖሊስ አሳውቀዋል ፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ትናንት ሰኞ የተገደሉት ማክዶናልድ በተባለ ሆቴል ውስጥ በመመገብ ላይ እንዳሉ ነው ፡፡

በደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ጥቃት በተደጋጋሚ ጊዜያት ይፈጸማል
በደቡብ አፍሪቃ መጤ ጠል ጥቃት በተደጋጋሚ ጊዜያት ይፈጸማል፤ እስካሁን ችግሩ መፍትኄ አላገኘምምስል፦ Getty Images/AFP/M.Safodien

ሥለግድያው ከእማኞች አንደበት

This browser does not support the audio element.

በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ ሦስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተመተው መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና የአገሪቱ ፖሊስ አሳውቀዋል ፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ ትናንት ሰኞ የተገደሉት ማክዶናልድ በተባለ ሆቴል ውስጥ በመመገብ ላይ እንዳሉ ነው ፡፡  ጥቃቱ የተፈፀመው መጤ ጠል አራማጅ ደቡብ አፍሪካዊያን በስደተኞች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት የሠልፍ ጥሪ እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው ፡፡

ሥለግድያው ከእማኞች አንደበት

ነዋሪነታቸው በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን እንደሚሉት ጥቃቱ ትናንት ሰኞ የተፈጸመው በከተማው ማክዶናል በተባለ ህንጻ ውስጥ ነው ፡፡ ኢትዮጵያዊኑ የተገደሉት ምግብ ለመመገብ ወደ ህንጻው በመግባት ተቀምጠው ባሉበት መሆኑን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሦስት በጆሃንስበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል ፡፡

ህንጻው ያለበት ሥፍራ small street ተብሎ በሚጠራ ጎዳና ላይ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሱት ኢትዮጲያዊያኑ " ሟቾቹ በዚሁ ጎዳና ላይ በከፈቷቸው ሱቆች ራሳቸውን የሚያስታዳድሩ ነበሩ ፡፡ ምግብ ለመመገብ ወደ ሆቴሉ ገብተው እንደተቀመጡ ነው እዚያው ተኩሰው የገደሏቸው ፡፡ ቦታው በጣም ጥብቅ የፀጥታ ጥበቃ ያለበት ነው ፡፡ በምን ድፍረት በዚህ ሥፍራ ግድያውን ለመፈጸም እንደቻሉ መገመት አስቸጋሪ ነው " ብለዋል ፡፡

የመጤ ጠል አራማጆች ቅስቀሳ

ጥቃቱ የተፈፀመው መጤ ጠል አራማጆች በፍልሰተኞች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት የሠልፍ ጥሪ እያደረጉ ባሉበት ወቅት መሆኑን ለዶቼ ቬለ አስተያየቱን የሰጠ አንድ ሌላ ነዋሪ በበኩሉ ከግድያው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ፖለቲከኞች " ወደ አገራቸው ይሂዱ " በማለት ፍልሰተኞች ላይ የሚያነሳሳ  ንግግር ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡ ከፖለቲከኞቹ በተጨማሪ  ነዋሪው  ሁሉም ባይሆን አብዛኛው የአገሬው ነዋሪ ለፍልሰተኞች የተዛባ አመለካከት እንዳለው አስተያየት ሰጪው ተናግረዋል ፡፡

የጆሐንስበርግ ከተማ በከፊል ከላይ ሲታይምስል፦ CELINE CLERY/AFP/Getty Images

" በደቡብ አፍሪካ የምንገኛ ኢትዮጵያውያን ረጅም ሠዓት ለፍተን የራሳችንን ጥሪት መያዝ ችለናል " ያሉት እኝሁ አስተያየት ሰጪ " ነገር ግን አብዛኛው የአገሬው ዜጋ የእኛን ሥራ ቀምተውናል የሚል ስሜት አላቸው ፡፡ ኢትዮጵያዊያን የትላልቅ የንግድ ድርጅት ባለቤት ሆነው ሲታዩ በተለይ በደቡብ አፍሪካዊያን ሥራ እጥ ወጣቶች ዘንድ ጥሩ ሥሜትን አልፈጠረም ፡፡ ይህም በየጊዜው የተለያዩ ምክንያቶችን ሰበብ በማድረግ ለተደጋጋሚ ጥቃት አጋልጦናል ፡፡ የመጤ ጠል ጥቃት ሰለባ እንድንሆን አድርጎናል " ብለዋል ፡፡

እውን ፖሊስ እንዳለው  ግድያው የእርስ በእርስ መጠቃቃት ይሆን ?

አንድ የፖሊስ መኮንን ግድያውን አስመልክተው SABC ለተባለው የአገሪቱ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ግድያውን ያደረሱት ሁለቱ ማንነታቸው ያልተወቁ ግለሰቦች ናቸው ብለዋል ፡፡

ግለሰቦቹ ወደ ማክዶናል መግባታቸውን የጠቀሱት የፖሊስ መኮንኑ " ካዛም ሦስቱንም በተመሳሳይ ሁኔታ ገድለው ወጥተዋል  ፡፡ በአካባቢው በርካታ ወንጀሎች ይፈጸማሉ ፡፡ በየሳምንቱ እርስ በእርስ የሚገዳደሉበት ሁኔታ መኖሩን ሪፖርት አለን ፡፡ የአካባቢውን ነዋሪ ደህንት ለመጠበቅ እና ለመነጋገር ነገ ረቡዕ ለሁሉም የሱቅ ባለቤቶች ጥሪ አድርጊያለሁ  ›› ብለዋል ፡፡

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በየጊዜው በሚደርስባቸው ጥቃቶች ለሞት መዳረጋቸው በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል ፡፡ መንግሥታዊ ካልሆነውና ከደቡብ አፍሪካ የማህበረሰብ ጥምረት ከተባለ ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑወቅት ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW