የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግብ
ሐሙስ፣ ጥር 6 2013
ማስታወቂያ
ሱዳን በኢትዮጵያ ሉዓላዊ የድንበር ግዛት ውስጥ ዘልቃ በመግባት ያደረገችው ወረራ ሁለቱ ሀገራት ለረጅም ጊዜ የገነቡትን የወዳጅነት ግንኙነት የበጠሰ፣ ዓለም አቀፍ ሕግንም የጣሰ አደገኛ አካሄድ ነው ተባለ።
የኢትዮጵያን የውስጥ ነባራዊ ሁኔታ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በሱዳን በኩል የተፈፀመው ይህ ድርጊት ለሁለቱ ሀገር ሕዝቦች ዘላቂ መልካም ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውም አስጊ መሆኑንም ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ምኁራን ተናግረዋል።
ክስተቱ ኢትዮጵያን ከጀርባ የመውጋት አዝሚሚያ የተስተዋለበት ነው ያሉት ምኁራኑ ችግሩ በሠላም እንዲፈታ የሚደረገው ጥረት እንዲጠናከር፣ ይህ ካልተሳካ ግን አፀፋ መውሰድ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የሱዳን ጦር ተጠናክሮ ወደ ውስጥ ድንበር ጥሶ እንደገባና ጉዳዩን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ትዕግስት መምረጧን ስትገልፅ የሱዳን ጦር በበኩሉ የራሱ የነበረ ቦታን መቆጣጠሩን እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዳልገባ እየተናገረ ነው።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ