1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያና አሜሪካ ወቅታዊ ግንኙነት ላይ የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 16 2017

የአሜሪካን ው/ጉ/ሚ ማርኮ ሩቢዮ ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ጋር ያደረጉት ውይይት፣ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚረዳ ነው ይላሉ አቶ አያና። ዶናልድ ትራምፕ፣”የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተገነባው፣ በአሜሪካ መንግሥት ገንዘብ ነው ሲሉ”በተደጋጋሚ የሚሰጡትን አስተያየት፣ አገሪቱ ከምትከተለው ቋሚ ፖሊሲ ለይቶ ማየት ያስፈልጋልም ብለዋል ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮምስል፦ Umit Bektas/REUTERS

የኢትዮጵያና አሜሪካ ወቅታዊ ግንኙነት ላይ የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየት

This browser does not support the audio element.

የኢትዬጵያና የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በየጊዜው የሚያደርጓቸው ውይይቶች፣የሃገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገለፀ።  የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ትናንት በስልክ ያደረጉትን ውይይት መነሻ በማድረግ ዶቼ ቬለ ያነጋግራቸዉ የፖለቲካ ተንታኛ አያና ፈይሳ፣ውይይቱ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ያለውን ቀጣይ አጋርነት የሚያመለክት ነዉ ብለዋል ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣”የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተገነባው፣ በአሜሪካ መንግሥት ገንዘብ ነው ሲሉ”፣ በተደጋጋሚ የሚሰጡትን አስተያየት፣ አገሪቱ ከምትከተለው ቋሚ ፖሊሲ ለይቶ ማየት እንደሚያስፈልግም አቶ አያና አመልክተዋል። 

ኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትስ፣ዲፕሎማሲያዊ፣ኢኮኖሚያዊና የጸጥታ ጉዳዮችን ያቀፈ፣ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አላቸው።የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነትከ120 ዓመታት በላይ በተሻገረው በዚሁ የሁለቱ አገራት ግንኙነት፣ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን በፀጥታ ጉዳዮች በተለይም በአፍሪቃ ቀንድ ሽብርተኝነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብራ ትሰራለች።
በሁለቱ አገራት ሹማምንት መኻከልም በየአገሮቻቸው እንዲሁም በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በየጊዜው ውይይት ይካሄዳል ። ከዚህ አኳያ፣ የዩናይትድ ስቴትስ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ትላንት ያደረጉት ውይይት፣ በሁለቱ አገራት መኻከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚረዳ ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኙ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድምስል፦ Ethiopian PM Office

ቀጣናዊ ጉዳዮች

" ቀጣናው ላይ ጠብ አጫሪ የሆኑ አካላት ሙከራዎች፣ከውስጥና ከውጭ  ያሉ ቀጥታም በእጅ አዙርም የሚደረጉ የግጭት ቅስቀሳዎችን፣ሉዓላዊነት  ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን፣የሃገር ጥቅምን ተጽዕኖ ስር ለማስገባት የሚደረግ ነገር፣ እንዲሁም  የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተለይ የባህር በር ከማግኘት ጋር ተያይዞ ያለውን የነበሩ ግንኙነቶች አሉ እና ይሄ በሰላማዊ መንገድ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መንግስት አቐም እንደሆነ ተደጋግሞ ተገልጿል። ከማርኮ ሩቢዮ ጋር የተደረገው ውይይት፣ይህንኑ የሚያሰምርና በንግግርና በቀጣናው  መረጋጋት ላይ በውይይት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው፣ በዚያም ላይ የአሜሪካ መንግስት አጋርነቱን ያሳየበት ነው።»
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር  በስልክ የተወያዩት፣ኢትዮጵያና ኤርትራ አንዳቸው ሌላያውን እየወነጀለና፣ ዛቻም እያሰማ በአካባቢው ውጥረት ባየለበት ጊዜ  መሆኑ ነዉ ።

የምጣኔ ሃብት ጉዳይ

የአሜሪካየውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ትናንት እንዳመለከተው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ጉዳይንም  አንስተው ተነጋግረዋል።  ይሄ  ውይይት፣ከአሜሪካ ጋር በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የበለጠ አብሮ ለመስራት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አቶ አያና አስረድተዋል። 
" በኢኮኖሚ አንፃር አድንቀዋል፣ ኢትዮጵያ ያደረገችውን አገር በቀል የኢኮኖሚ መሻሻያና ያስገኛቸውን ውጤቶች አድንቀዋል የሚል ነው መግለጫቸው።ይኼ ደግሞ ሌሎች ዕድሎች እንዳሉ በተለይ በንግድና በ ኢንቨስትመንት ከአሜሪካአጋር አብሮ ለመስራት ዕድሎችን  እንደሚፈጠር ነው የሚገልጸው።ከአሜሪካ ጋር አብሮ ለመስራት ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ያመላከተ ነው የስልክ ውይይታቸው።"

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ ጋር በዋይት ሀውስ ሲነጋገሩምስል፦ Stringer/Sputnik/IMAGO

 በሕዳሴ ግድቡ ላይ ለትራምፕ ምላሽ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተገነባው በአሜሪካ ገንዘብ ነው በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸውን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የፖለቲካ ተንታኙ እንደሚከተለው መልሰዋል።
 "ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አንዳንድ ጊዜ በመድረክ የሚናገሯቸውና የአሜሪካ ቋሚ የሆነ ፖሊሲና አፈፃፀምን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል። የአሜሪካን ፖሊሲ በተመለከተ፣ያላቸው አቋም ከዚህ በፊት ከነበሩት የአሜሪካ ኘሬዚዳንቶች እምብዛም የተለየ አይደለም።ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት እኛ ነን አስተዋጽኦ ያደረግነው ነው የሚሉ አንዳንድ ነገሮች፣ የሚታወቁ እውነትነት የሌላቸው ነገሮች ይናገራሉ። ራሳቸውን ብዙ ስምምነት እንደሚፈጥሩ ያሳያሉና ይሄ የተለመደው የእርሳቸው ባህሪ ነው። እውነትን የሚያጠሩ ጋዜጠኞች ብለው ብለው ከተዉዋቸው ቆይተዋልና፣ ትንሽ ወጣ ያለ አቀራረብ ነው ያላቸው።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ 
አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW