የኢትዮጵያና የሱዳን ኃይላት ቁርቁስ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 8 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያና የሱዳን ወታደሮች ወይም ታጣቂዎች አንዳቸዉ የሌላቸዉን ድንበር አልፈዉ ጥቃት ማድረሳቸዉን ሁለቱ ወገኖች በየፊናቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የአማራ ክልል ባለስልጣናትና የሰሜን ጎንደር የአርማ ጮኾ ነዋሪዎች እንደሚሉት የሱዳን ታጣቂዎች ባለፈዉ ማክሰኞ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረዉ ታች አርማጮኾ አካባቢ ባደረሱት ጥቃት ሕይወትና ንብረት አጥፍተዋል።ጥቃት አድርሰዋል።የሱዳን መንግስት በበኩሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሱዳን ግዛት ተሻግረዉ በከፈቱት ጥቃት አራት ወታደሮቹ መገደላቸዉን ትናንት አስታዉቆ ነበር።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ