1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?

Eshete Bekele
እሑድ፣ ጳጉሜን 3 2016

በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት እና መንግሥት ምን ሊያደርጉ ይገባል?

DW TV-Bericht  | Äthiopien | Vergewaltigung als Waffe im Tigray Konflikt
በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ከሚገኝ ሴቶች መካከል 10 በመቶው ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ከጥቂት ዓመታት በፊት ይፋ ያደረገው አንድ ሰነድ ያሳያል።ምስል DW

የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?

This browser does not support the audio element.

በሔቨን አወት ጉዳይ የተቀሰቀሰው በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት ለተፈጸመባቸው ሴቶች ፍትኅ እንዲሰጥ የሚደረገው ውትወታ የመቀዛቀዝ አዝማሚያ አሳይቷል። በባሕር ዳር ከተማ በኃይል ከተደፈረች በኋላ ሕይወቷ ያለው የሰባት ዓመቷ ሔቨን ጉዳይ መነጋገሪያ የሆነው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባለው ተከሳሽ ይግባኝ መጠየቁ ከተሰማ በኋላ ነው።

በኢትዮጵያ እንደ ሔቨን ሁሉ ብርቱ ገነነ፣ ፋጡማ ኡጋስ፣ ጫልቱ አብዲ ፣ ሐና ላላንጎ እና ፀጋ በላቸውን የመሳሰሉ ሕጻናት፣ ወጣቶች እና አዋቂ ሴቶች ተመሳሳይ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ከሚገኝ ሴቶች መካከል 10 በመቶው ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ከጥቂት ዓመታት በፊት ይፋ ያደረገው አንድ ሰነድ ያሳያል።

የትግራይ፣ አማራ እና የአፋር ክልሎችን ያዳረሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ግጭቶች ወሲባዊ ጥቃት እንዲስፋፋ አድርገዋል። ግጭቶቹ አስተዳደራዊ መዋቅሮችን እና የጸጥታ ተቋማትን በማዳከማቸው አጥፊዎች ተገቢውን ቅጣት እንዳያገኙ አስተዋጽዖ እያደረጉ ነው።

ለመሆኑ ወሲባዊ ጥቃት ለተፈጸመባቸው ፍትኅ እንዲሰጥ ይደረግ የነበረው ውትወታ ምን ያህል ውጤታማ ሆነ? ችግሩስ ምን ያክል አሳሳቢ ነው? የሀገሪቱ ሕግ ለተበዳዮች ፍትኅ ማረጋገጥ ለምን ተሳነው? ወሲባዊ ጥቃትን ለማስቆም ማን ምን ማድረግ አለበት?

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ለውይይቱ ተሳትፈዋል።

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፦

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW