1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያውያን መከራ በሱዳን

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 3 2014

ጎረቤት አገር ሱዳን ያሉ ኢትዩጵያውያን በአብዛኛው ሰቆቃ እንደሚፈጸምባቸው፣ እንደሚገረፉና በየእስር ቤቱ እንደሚታጎሩ፣ እንዲሁም ሴቶች እንደሚደፈሩ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከአራት ዓመት በላይ የኖረችው አልማዝ ከሁለት ዓመት ወደዚ ያለው ጊዜ በጣም አስፈሪ ነው ትላለች

Karte Sudan Äthiopien EN

በርካቶች እንደታሰሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል

This browser does not support the audio element.

በርካታ ኢትዮጵያውን በተለይም ወጣቶች በኢመደበኛ መንገድ ድንበር አቋርጠው መሰደድ ከጀመሩ በርካታ ዐሠርተ ዓመታት ተቆጥረዋል። ጉዞ ተሳክቶላቸው ከአንዱ አገር የደረሱት ደግሞ ለጉልበት ብዝበዛ አሊያም ለእስር መዳረጋቸው የተለመደና በየጊዜው የሚነገር ክስተት ነው፡፡ ይህም ሆኖ ዛሬም በርካታ ኢትዮጵያውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ችግራቸውን ለማምለጥ ከተሳካ በመደበኛ፣ ካልተሳካ በኢመደበኛ መንገድ ድንበር አቋርጠው ይሰደዳሉ።

ጎረቤት አገር ሱዳን ያሉ ኢትዩጵያውያን በአብዛኛው ሰቆቃ እንደሚፈጸምባቸው፣ እንደሚገረፉና በየእስር ቤቱ እንደሚታጎሩ፣ እንዲሁም ሴቶች እንደሚደፈሩ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከአራት ዓመት በላይ የኖረችው አልማዝ ከሁለት ዓመት ወደዚ ያለው ጊዜ በጣም አስፈሪ ነው ትላለች። ከመንገድ ላይም ይሁን ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍሰው የታሰሩ ኢትዩጵያውያን በጣም በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ናቸው እራሳቸውን ያጠፉም እንዲሁም የተደፈሩ አሉ ትላላች።

«ሱዳን ላይ ያለው ችግር በጣም አስከፊ እና አስፈሪ ነው» የምትለው አልማዝ አፈሳ ከጀመረ ሁለት አመት ሆኖታል ለማን አቤት እንደምንል እራሱ ግራ ገብቶናል። ኤምባሲው ሲጠየቅ ሕጋዊ መሆን አለባችሁ የመኖሪያ ፈቃድ አውጥታችሁ ነው መኖር ያለባችሁ ነው የሚለን መፍትኄ አፈለልጉልን ሥራ መውጣት አልቻልንም መንገድ ላይ እየተያዝን ነው»። ስትል እስር ቤት ስለታሰሩት እንዲ ብላለች እስር ቤት ብዙ ሰው የታሰረው ሴቶች እየተደፈሩ ነው ወንዶች ብር አንከፍልም ያሉትን  የት እንደሚወስድዋቸው አናውቅም። እስር ቤት ውስጥ ሁለት ወንዶች እራሳቸውን አጥፍተው ሞተዋል።  እኛ ግራ ገብቶናል ለማን አቤት እንደምን። ስንት እህቶች ወንድሞቻችን የት እንደደረሱ አዐናውቅም። ምን እንደሚያደርጉዋቸው ዐናውቅም፤ መንግስት በተቻለው መጠን ወደ አገራችን እንዲያስገባን ነው የምንጠይቀው ሌላ ምንም አልፈልግም » ብላለች።

ሌላው በሱዳን ለዓመታት የኖረው ኢትዩዮጵያዊው ዳንኤል ተስፋሁን   መንግስት አንድ መፍትሄ ፈጥሮ ወደ አገራችን የምንገባበትን መንገድ ይፈልግልን ሲል  ቁጥራቸው በርካታ ሴቶች  ከነ ልጆቻቸው በእስር ላይ ናቸውም ሲል አክሏል። ኤምባሲ ተመላልሰን አመልክተናል ግን አጥጋቢ መልስ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም ሲል ለዶቼ ቬሌ ተናግርዋል። 

«አፈሳው የጀመረው የዛሬ ሁለት አመት አካባቢ ነው  ፖሊሶች በጣም እያሰቃዩን ነው። እስር ቤት ከገባሽ በኋላ እራሱ ብር ከፍለሽ ወጥተሽ ቤትሽ ሳትደርሺ የሚይዙበት አጋጣሚ ነው ያለው። ኤምባሲ ስናመለክትም ሕገወጥ ናችሁ የአገሩ ሕግ ነው ምንም ማድረግ አንችልም ይላሉ»እኛ ምንም አንፈልግም መንግስት ወደ አገራችን ምንመለስበትን መንገድ እንዲያመቻችችልን ብቻ ነው የምንፈገው ኢል ቀጥሎም  «ሴቶች አሁን በብዛት ከነልጆቻቸው ነው የታሰሩት። እስር ቤትም እየተደፈሩ ነው» ብልዋል በእግር ወደ አገራችን እንዳንመለስ   በፀጥታ ችግር ምክንያት መንገዱ ተዘግትዋል ያለው ዳንኤል  በኮንትሮባንድ እንኩዋን እንግብባ ብንል ክፍያው ብዙ ነው ብልዋል   አሁን ከቤቱ የሚወጣ ሰው የለም ሁሉም ቤቱ ነው ቁጭ ብሎ ነው ያለውያለው ዳንኤል ። «እኛ ኢትዮጵያውያን ካልሆንን ኤምባሲ ይንገረን።» ሲል ለዶቼ ቬሌ ተናግርዋል።

በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ በአሁኑ ሰአት ኢትዮያውያን ላይ የሚደርሰውን እስርና እንግልት አስመልክቶ ኤምባሲው ምን እያደረገ እንደሆነ በስልክ ጠይቀናቸው በርካታ ኢትዩጵያውያን ሰነድ አልባ ናቸው  የመኖሪያ ፈቃድ ሆነ የስራ ፈቃድ የሌላቸውና በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ ናቸው ብለዋል በአሁኑ ሰአት ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጋ ኢትዮጵያው በሱዳን አሉ ብለዋል አክለውም «በትንሹ 90% የሚሆነው ኢትዩጵያዊ ሕገ ወጥ ነው። ፓስፖርት የላቸውም አሁን ላይፓስፖርት የሚያገኙበትን ሁኔታ እያመቻቸን እንገኛለን»ሲሉ ሌላው ዜጎች የሚጠይቁት  አገራችን መመለሻ መንገድ ይከፈትልን ነው ለዚ ደሞ በመኪና ለሚሄድአሁን ላይ መንገዱ ክፍት ነው ብለዋል  በእስር ላይ ስላሉት ዜጎች ለቀረበላቸው ጥያቄ  እኛ እየተከታተልን ነው ወደ እስር ቤት እንሄዳለን ባለስልጣናትን እናናግራለን ከዚ በተጨማሪ ደሞ ባለስልጣናቱ እንዲታገሱን በመጠየቅ በማግባባት ላይ ነን ሲሉ ። ዜጎች አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን አልደበቁም «ዞሮ ዞሮ ዜጎቻችን ችግር ላይ ናቸው ሱዳን ላይ ያለው የኑሮ ውድነት እራሱ ሌላው ችግር ነው  ብለዋል እስር ቤት ስለተደፈሩ ሴቶች በተመለከተ  በአስተዳደራዊ ደረጃ የሚፈጠሩ ችግሮች እንደሚኖሩ እንረዳለን ግን መሆን የለበትም ከባለስልጣናት ጋር ስንገናኝ የምናነሳው ይሆናል» ብለዋል። «ኤምባሲው ሌላ ምንም ስራ የለውም ሥራችን  የዜጎቻችን መብት ማስከበር ነው» ብለዋል።

አምባሳደር  ይበልጣል አእምሮ አክለውም  ኤምባሲው ለዜጎቹ መብት እየታገለ ቢሆንም በአንድ አገር አሠራር ላይ ግን ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተናግረዋል። በሱዳን ግን አሁንም የኢትዮጵያውያኑ እስር እንደቀጠለ ነው። ሱዳን ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል ሰሞኑን ከዶይቸ ቬለ በስልክ ደውለን ያነጋገርናቸው ሁለት ሰዎች መታሰራቸውን ጓደኞቻቸው ነግረውናል።

ማህሌት ፋሲል 

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW