1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጲaweያን ስደተኞች መቃብር በማላዊ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 10 2015

የማላዊ ፖሊስ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የሞቱት በተሸፈነ መኪና ሲጓዙ በአየር እጥረት ታፍነው ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ይጠረጥራሉ።

Infografik Karte Malawi EN

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መቃብር በማላዊ

This browser does not support the audio element.

በማላዊ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ናቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰዎች የተቀበሩበት መቃብር በአንድ ጫካ ማግኘቱን  የሃገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።  ስደተኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ የገለጸው ፖሊስ የሞቱበትን  ምክንያት ግን አላስታወቀም።ፖሊስ እንዳለዉ የሟቾቹ ቁጥር ከ25 እስከ 30 ይገመታል።

በማንጋታንጋ ጫካ ተቀብረው የተገኙት  ስደተኞች እድሜያቸው ከ25 እስከ40 ዓመት የሚገመት  እንደሆኑ የማላዊ ፖሊስ ቃልአቀባይ ፒተር ካላያን ተናግሯል።ቃል አቀባዩ እንዳሉት ሟቾቹ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሳይሆኑ አይቀርም። የመሞታቸው ምክንያት ግን  ገና እየተጣራ መሆኑን አስታዉቀዋል።

```እስካሁን ከቦታው  ያሰባሰብነው መረጃ እንደሚያመለክተው ሟቾቹ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ጉዳዩን በመመርመር ላይ ነው ያለነው።   ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባልደረቦቻችን የሟቾቹን ሞት ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ሪፖርት እንዲያቀርቡልን እየጠበቅን ነው። ሟቾቹ ምናልባትም እኛ እንደምንጠረጥረው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ያቀዱ ሊሆኑ ይችላሉ። ምክንያቱም በዛ አካባቢ በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት ነገር ስለሚያጋጥም።``

የአካባቢው የማህበረሰብ ራድዮ ጋዜጠኛ ናዋሚ ጀሬ የሰዎቹን ማንነትና አሟሟታቸዉን ኅብረተሰቡ ሊረዳው ስላልቻለ ሁኔታው  ውጥረት ፈጥሮ ነበር ብላለች

`` ባካባቢው ያለው ማህበረሰብ መቃብሩን ሲመለከት በጣም አዝኖ ነበር። የሞቱት ሰዎች የማህበረሰቡ አባላት መስሏቸው ነበር። ፖሊስ አጣርቶ አስከሬኑ የውጭ ዜጎች መሆኑን ሲገልጽ ግን እፎይታ አስገኝቷል።``

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የሞቱት በተሸፈነ መኪና ሲጓዙ በአየር እጥረት ታፍነው ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ይጠረጥራሉ።

ባለፈው ሃምሌ ወር የሃገሪቱ ፖሊስ በአንድ ሽፍን የጨነት መኪና 42 ኢትዮያውያን ስደተኞች ይዞ የነበረ ሲሆን ከጥር እስከመስከረም ባለው ጊዜ በታንዛንያና ማላዊ ድንበር ባለው መስመር በተመሳሳይ ከተያዙ 221 ስደተኞች 186ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን በማላዊ የዶይቸቬለ ወኪል የላከልን ዘገባ አመልክቷል።

 ሚሪያም ካሊዛ/ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW