1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላምና ዕርቅ ለኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 15 2016

የዕርቅና የድርድር መንገድ በማመቻቸት ሰላም የሚገኝበትን ሁኔታ ለመፍጠር መነሳሳታቸውን የድርጅቱ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሲሣይ አሰፋ ገልጸዋል።ጦርነቶቹን በሰላማዊ መንገድ በአፋጣኝ ለማስቆም አባላቱ መንግስትንና ተፋላሚ ኀይላቱን የሚያነጋግሩ ልዑካንን መርጠው በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።

 «አንደኛው ዲያስፖራውን በሙሉ ማሰባሰብ ነው። ሁለተኛው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጦርነትማስቆምና ሰላም ማምጣት ነው። ሦስተኛው ሁላችንም እንደምናምነው፣ ዲያስፖራው ብዙ ሪሶርስ አለው።ያንን ለሀገራችን ዕድገትና ሰላም ዘለቄታዊ ሁኔታ የምንሰባራበትን ማዘጋጀት ነው።»
ከፔንሲልቫኒያ አሜሪካ የጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃኑ ውርሴኖ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ ሦስት ዓላማዎችን አንግቦ መነሳቱን ያስረዳሉ። ምስል Ato Birhanu Wurseno

«የኢትዮጵያውያን አንድነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት ድርጅት» የሰላም ጥረት

This browser does not support the audio element.

ለኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ጦርነቶችን በአፋጣኝ ማስቆም እንዲቻል የሰላምና ዕርቅ ጥረት መጀመሩን የኢትዮጵያውያን አንድነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ዕድገት ድርጅት አስታወቀ። በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው የድርጅቱ ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ፕሮፌሰር ሲሳይ አሰፋና አቶ ብርሃኑ ውርሴኖ በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት፣ ጦርነቶቹን በአስቸኳይ ለማስቆም መንግስትንና ተፋላሚ ኀይላትን የሚያነጋግሩ የሰላም ልዑካን ቡድን አባላት ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። ወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ፣መላውን የሃገሪቱን ህዝብና ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ጭምር የሚያሳስብ እንደሆነ፣የኢትዮጵያውያን አንድነት ለኢትዮጵያ ሰላምና እድገት ድርጅት ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ይናገራሉ። የወደፊት የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? የሚል ስጋት እንደፈጠረባቸውም አመልክተዋል።ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ ማፈላለግ እና የሲቪክ ማህበረሰብ ሚና

በመሆኑም የዕርቅና የድርድር መንገድ በማመቻቸት፣ሰላም የሚገኝበትን ሁኔታ ለመፍጠር መነሳሳታቸውን የድርጅቱ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሲሣይ አሰፋ ገልጸዋል። «በቅርቡ ነው የተጀመረው፤በሰላምና ዕድገት ላይ ነው።ዕድገት ከመኖሩ በፊት ሰላም ያስፈልጋል።ፖለቲካ ውስጥ አንገባም።ሠላም እንዲኖር በኢትዮጵያ፣ዋናው ነገር በተቻለ መጠን ጦርነት ማቆም ነው።»ከፔንሲልቫኒያ አሜሪካ የጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃኑ ውርሴኖ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ ሦስት ዓላማዎችን አንግቦ መነሳቱን ያስረዳሉ። «አንደኛው ዲያስፖራውን በሙሉ ማሰባሰብ ነው። ሁለተኛው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጦርነትማስቆምና ሰላም ማምጣት ነው። ሦስተኛው ሁላችንም እንደምናምነው፣ ዲያስፖራው ብዙ ሪሶርስ አለው።ያንን ለሀገራችን ዕድገትና ሰላም ዘለቄታዊ ሁኔታ የምንሰባራበትን ማዘጋጀት ነው።»የኢጋድ የሰላም ጥረት በኢትዮጵያ

ጦርነቶቹን በሰላማዊ መንገድ በአፋጣኝ ለማስቆም እንዲቻል፣ የጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላቱ፣መንግስትንና ተፋላሚ ኀይላቱን የሚያነጋግሩ ልዑካንን መርጠው በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። "ልዑካንን መርጠን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዝግጅት ውስጥ ነው ያለነው። እና አካሄዳችን ዞሮ ዞሮ ሰላም ለመፍጠር ነው።በመጀመሪያ ጦርነቱን የማስቆም ጉዳይ ነው።ከዚያ በኃላ ደግሞ፣ቋሚ የሆነ ዘላቂ ሰላም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመጣ የሚችልበትን ነገር ከመንግስት ጋር አብረን ለመስራት ነው።" ልዑካኑ መንግስትን ጨምሮ የፋኖ፣ የኦነግና የህወሓት መሪዎችን ለማነጋገር ማቀዳቸውን የጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላቱ አስታውቀዋል። የሰላም ልዑክ አባላቱ፣ገለልተኛ የሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ በበጎ የሚታዩና ለሰላምና ለዕርቅ ባላቸው ችሎታ፣ተቀባይነት ያላቸው እንዲሁም ሚስጥር ለመጠበቅ የሚችሉ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል። ወደ ኢትዮጵያ የሚሄደው ይኸው የሰላም ልዑክ፣ከኀይማኖት ተቋማት መሪዎች፣በሃገር ዉስጥ ለሰላም ከሚሰሩ ድርጅቶችና ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ጋር ተቀናጅቶ እንደሚሰራም ጠቁመዋል። ዝርዝር አሰራሩም፣ በምክክር ተዘጋጅቶ በቀጣይም ሰነድ የሚቀርብ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

ታሪኩ ኃይሉ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW