1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የድጋፍ ሰልፍ በፓሪስ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 14 2010

ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ዛሬ በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ በጋራ ሰልፍ ወጥተዋል። ሰልፉ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

Ethiopians and Eritreans rally
ምስል Haimnot Tiruneh

የኢትዮ- ኤርትራ የድጋፍ ሰልፍ በፓሪስ

This browser does not support the audio element.

በዛሬው የፓሪስ የድጋፍ ሰልፍ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ አምባሳደሮች ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ በኩል በፈረንሳይ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑት አሊ ሱሌማይን እና የኤርትራው አቻቸው አምባሳደር ሐና ስምዕን በሰልፉ ላይ ተካፍለዋል። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን መፈክሮችን አንግበው፤ ባንዲራቸውን እያውለበለቡ ድጋፋቸውን ሲገልጹ ታይተዋል። በፓሪሱ ሰልፍ ከኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በተጨማሪ የሌሎች አፍሪቃ ሃገራት ዜጎች የየሀገራቸውን ባንዲራ በመያዝ ደስታቸው ገልጸዋል።   

ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ የፓሪሱን ሰልፍ ተከታትላለች። የሰልፉን ድባብ በተመለከተ ከእርሷ ጋር የተደረገው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ከታች የድምፅ ማዕቀፉ ውስጥ ይገኛል።  

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW