የኢትዮጵያውያን ዴያስፖራ ማሕበረሰብ አስተዋጽዖ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 22 2014![Äthiopien medizinische Hilfe](https://static.dw.com/image/60303642_800.webp)
ማስታወቂያ
አዲሱን የፈረንጆች ዓመት እና የኢትዮጵያ ገናን ምክንያት በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ በመንግስት ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አገር ቤት እየመጡ ነው፡፡
ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያኑ በሰሜን የአገሪቱ አከባቢዎች በጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን፤ በተለይም የህክምና ተቋማት ውድመትን ወደ ነባር ይዞታው ለመመለስ ይረዳል ያሉትን የህክምና ቁሳቁሶች ይዘው እየመጡ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ያነጋገራቸው ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ አንድ የጀርመን ነዋሪ እንደሚሉት ኢትዮጵያውያን አንድነትን ከፈጠሩ ለአገራቸው በርካታ ቁምነገሮች ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡
አንድ የዲፕሎማሲ ተንታኝ በፊናቸው እንደሚሉት የኢትዮጵያውያኑ በአገራቸው ጉዳይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ የአገራቸውን ጥቅም ከማስከበር አንጻር ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ