1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ብሪታኒያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ያካሄደው ውይይት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 4 2018

በምክከሩ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ተፉላሚ ኃይሎች ተካፍለዋል ወይ እነሱ ያልተካፈሉበት አገራዊ ምከክር ምን መፍትሄ ያመጣል የሚል ጥያቄም ተነስቷል። በእለቱ ከመወያያው አዳራሽ በር ላይ አያሌ የአማራ ፉኖ ኃይል ደጋፊዎች ጦርነት እየተካሄደ ንፁሀን ዜጎች እየተገደሉ ባለበት ወቅት ውይይቱ ተገቢ እይደለም ሲሉ ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር።

ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቅዳሜ በብሪታኒያ  ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ያካሄዱት ውይይት
ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቅዳሜ በብሪታኒያ  ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ያካሄዱት ውይይት ምስል፦ Delnesaw Getaneh/DW

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ብሪታኒያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ያካሄደው ውይይት

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ አፍሪካ በዱባይ በካናዳ በአሜሪካ በስዊድን ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ካጠናቀቁ በኋላ ቅዳሜ ደግሞ  በብሪታኒያ  ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሀገራዊ ምክክር ሂደት ባለ ድርሻ ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን ባገራቸው ጉዳይ ላይ ይጠቅማል ያሉትና ይበጃል ያሉትን ጠቃሚ ሃሳብ ለማሰባሰብና የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎችን ለማስመረጥ ጭምር መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ለታዳሚው ህዝብ ገልፀዋል። የኮሚሽኑ ዋናውና መሰረታዊ አላማው ራዕይ በኢትዮጵያ  መግባባትን በመፍጠር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አገር እንድትሆን መሠረት ለመጣል እንደሆነ አብራርተዋል 

የኮሚሽኑ አባላት በሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራውንና በህዝብ የተሰጠውን አደራ እውን ለማድረግ ከጀመረበት ጊዜ እስካሁን ድረስ 3200 መድረኮችን በማዘጋቸት ህዝብን በማወያየት በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶች መፍትሄ ለመሻት የተቻለውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።  በእለቱ ከብሪታንያ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ 11 ተሳታፊዎችን ከተለያዩ የሙያ ዘርፍ  ተመርጠዋል።

በምክከሩ ወቅት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ተፉላሚ ኃይሎች ተካፍለዋል ወይ እነሱ ያልተካፈሉበት አገራዊ ምከክር ምን መፍትሄ ያመጣል በሚል ለተነሳው ጥያቄ ምከትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ማብራሪያ ሰጥተዋል።ምስል፦ Delnesaw Getaneh/DW

በምክከሩ ወቅት ብዙ የተነሱ ጥያቄዎች ነበሩ ከነዚህም መካከል የተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎችና ተፉላሚ ኃይሎች ተካፍለዋል ወይ እነሱ ያልተካፈሉበት አገራዊ ምከክር ምን መፍትሄ ያመጣል በሚል ለተነሳው ጥያቄ ምከትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በአማራ ክልልና በሌሎችም ክልሎች ስለ ሚገኙ ተፉላሚ ኃይሎችን በተመለከተም ምክትል ኮሚሽነሯ ገለጻ ሰጥተዋል።  
በእለቱ የምክክር ኮሚሽኑ ውይይት ከሚያደርግበት የስብሰባ አዳራሽ መግቢያ በር ላይ አያሌ የአማራ ፉኖ ኃይል ደጋፊዎች  ጦርነት እየተካሄደ ንፁሀን ዜጎች እየገደሉ ባለበት ወቅት ውይይቱ ተገቢ እይደለም በማለት ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር። የተወሰኑም ተቃዋሚዎች አዳራሹ ውስጥ በመግባት በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግድያ ይቁም በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል'። 
በትላንትናው እለት የኮሚሽኑ ልኡካን በብሪታኒያ በአለም አቀፍ በእርቀ ሰላም ድርድር ስራ ከሰሩና ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ድልነሳው ጌታነህ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW