1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጥሪ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 19 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ በሦስት ክልሎች የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዐስታወቀ ። ከመጋቢት 11 እስከ 25 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ድረስ በደቡብ ፣ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ሦስት ዞኖች ውስጥ 142 ሺህ 575 ሰዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉም ብሏል ።

Äthiopien Ombudsman
ምስል፦ Solomon Muche/DW

«የመንግሥት ተሿሚዎች ርዳታ የሚቀራመቱበት ቦታ አለ»

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ውስጥ በሦስት ክልሎች የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዐስታወቀ ። ተቋሙ አሰባሰብሁት ባለው መረጃ መሰረት ከመጋቢት 11 እስከ 25 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ድረስ በደቡብ ፣ በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ሦስት ዞኖች ውስጥ 142 ሺህ 575 ሰዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ ።  የመንግሥት አመራሮች ሳይቀር በተረጂነት ስም እንደሚቀራመቱት በቁጥጥር ሥራው ማረጋገጡን ገልጾ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ሌሎች አካላት እርምት እንዲደረግ እንዲያደርጉ ጠይቋል ። የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ቁጥጥር ባደረገበት የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ በተጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሞተ ሰው ስለመኖሩ ማረጋገጫ አለማግኘቱን ያስታወቀው የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ከ1.7 ሚሊየን በላይ እንስሣት ማለቃቸውን ገልጿል ።  

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጎርፍ እና ድርቅ ችግር ላይ ለጣላቸው ዜጎች የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ ወቅቱን ጠብቆ የማይደርስ፣ ፍትሓዊነት የሚጎድለው ከመሆኑም ባለፈ ድርቅ ከአምስት ዓመታት በላይ በመታቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ከደረሰው የእንስሣት እልቂት ባለፈ በዝናብ እና በጎርፍ ምክንያት ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ መኖሪያ ቤቶች ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ ጤና ኬላዎች እና ሌሎችም መሠረታዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውድመት ደርሶባቸዋል ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ አባላትምስል፦ Solomon Muche/DW

ዘላቂ የድርቅ እና ጎርፍ መከላከል ስልት ተነድፎ መፍትሔ አለመሰጠቱ ይህንን ማስከተሉን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል ። በተቋሙ የአስተዳደር በደሎች መከላከል ዳይሬክተር አዳነ በላይ መጋቢት ላይ ያደረጉትን የቁጥጥር ሥራ የቦረናውን በመዘርዘር የጀምራሉ ። ከመጋቢት 11 እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ለሁለት ሳምንታት ድረስ እንባ ጠባቂ አደረግሁት ባለው ቁጥጥር ለጉዳዩ ትኩረት ካለመስጠት ፣ ግልጽ የመረጃ ልውውጥ ካለመኖሩ ባለፈ የመንግሥት ተሿሚዎች ርዳታ የሚቀራመቱበት ቦታ መኖሩንም አመልክቷል ።  

በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ሞት ያስከተለው፣ በንብረት ላይ አያሌ ውድመት ያስከተለው የተፈጥሮ አደጋ የሰው ሕይወት ላይስ ብለን ጠይቀን የእንባ ጠባቂ ተቋሙ የለም የሚል መልስ ሰጥቷል ። በተቋሙ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ደረጀ ተሊል ። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተፈጥሮ አደጋ በደረሰባቸው አካባቢዎች ለመልሶ ማቋቋም ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውለው በጀት እንዲጠና እንዲሁም ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈለግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ሌሎች የመንግሥት አካላት ጥሪ አድርጓል ።

ሰለሞን ሙጬ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW