የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት
ዓርብ፣ ኅዳር 28 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያን ሕገ-መንግሥት የማስከባሩ ሐላፊነት ከሐገሪቱ መንግሥት ይልቅ የመብት፥ ነፃነት ተሟጋቾችና ሐላፊነት የሚሰማቸዉ ወጣቶች የመሆኑ እንቆቅልሽ ገሐድ እየወጣ ነዉ።ዞን-ዘጠኝ በሚል መጠሪያ የተደረጁ የድረ-ገፅ ወጣቶት ታዳሚዎች ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበትን አስራ-ስምተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ «ሕገ-መንግሥቱ ይከበር» የሚል ዘመቻ ትናንት ጀምረዋል።መንግሥት ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ በሐይማኖታዊ ጉዳያችን ጣልቃ ገብቷል የሚሉት ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞችም ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር አበክረዉ እየጠየቁ ነዉ።የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለይ የሐይማኖት ነፃነት የተደነገገበት አንቀፅ ሃያ-ሰባት መጣሱን አዉግዘዋል።ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ዮሐንስ ገብረ-እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ