1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንን ይዞታ የቃኘው ውይይት

ሐሙስ፣ የካቲት 16 2015

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀንን የአሠራርና የአዘጋገብ ዳሰሳ እንዲሁም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የግጭት አገናዛቢ አርትኦት ፖሊሲዎችና አተገባበራቸው በሚል ርዕስ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች አዲስ አበባ ላይ ቀርበዋል። በየመብቶች እና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል አማካኝነት ለውይይት የቀረቡት ሁለቱ ጥናታዊ ጽሑፎችም በዘርፉ ባለሙያዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Äthiopien I Massenmedien Forschungsbuch Lounch
ምስል Hanna Demissie

«ሁለት ጥናት ለውይይት ቀርቧል»

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀንን የአሠራር እና የአዘጋገብ ዳሰሳ እንደዚሁም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የግጭት አገናዛቢ አርትኦት ፖሊሲዎች እና አተገባበራቸው  በሚል ርዕስ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች  አዲስ አበባ ላይ ቀርበዋል። በየመብቶች እና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል አማካኝነት ለውይይት የቀረቡት ሁለቱ ጥናታዊ ጽሑፎችም በዘርፉ ባለሙያዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሁኔታን የቃኘ «ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የግጭት አገናዛቢ አርትኦት ፖሊሲዎች እና አተገባበራቸው» የሚል የመነሻ ጥናት እና «የግጭት አገናዛቢ አዘጋገብ ዳሰሳ በኢትዮጵያ» በሚመለከት  ሁለት ጥናታዊ  ጽሑፎች  በየመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከከል አማካኝነት ለውይይት ቀርበዋል። ትናንት ይፋ በሆኑት በእነኝህ ሁለት ጽሑፎች አማካኝነትም ባለፍት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ የነበረችበትን ምህዳር በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙኃን ተግዳሮት እንደዚሁም ተቋሞቹ ከአድማጮች ተመልካቾቻቸው ጋር በምን መልኩ ደርሰዋል የሚለውን በስፋት ለመዳሰስ ሙከራ አድርጓል።

ምስል CARD

ከጥቂት ዓመታት በፊት የዓለም የፕረስ ቀንን በምድሯ ያከበረችው ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እየታሠሩ፣ የህትመት ውጤቶች እየመነመኑ እና ሚዛኑን የጠበቀ መገናኛ ብዙኃን ማየት እየቸገረ የመምጣቱን ምክንያት ምን እንደሆነ አቶ ፍቃዱ ሀይሉ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ኃላፊ ተናግረዋል። 

በጥናቱ እስካሁን ወደ 60 የሚሆኑ ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ሁለት ጋዜጠኞች ሕይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል። «ጋዜጠኞች አንዱን ወገን ካልያዙ መሥራት በተቸገሩበት ወቅት ሚዛናዊ ሆኖ መሥራት ፍፁም አስቸጋሪ ሆንዋል፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ አወቃቀር ካልተስተካከለ በቀር» ሲሉ ለዶቼ ቬለ/ DW/ የገጹት ደግሞ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ናቸው።

በውይይቱ ላይም የኢትዮጵያ መገንኛ ብዙኃን ከ2018 በኋላ ምን ይመስላል የሚለው ምልከታ ወደ ፊት ምን መደረግ እንዳለበት ለመነጋገር እና መፍትሄ ለመፈለግ ምክንያት ይሆናል ነው የተባለው። በኢትዮጵያ ያሉትን 117 የመገናኛ ብዙኃንን የሥራ እና የአዘጋገብ ሁኔታ በስፋት የዳሰሰው ጥናታዊ የጽሑፍ አቅራቢዎች ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ሞገስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ሁኔታ አቶ ወንድወሰን ንጉሤ «የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የግጭት አገናዛቢ አርትኦት ፖሊሲዎችና አተገባበራቸው» በሚል ባቀረቧቸው ጽሑፎች ከመድረኩ ተወያዮች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

 ሃና ደምሴ  

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW