የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ መታገድ
ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሙስሊሞች በየሳምንቱ አርብ ከሶላት በኋላ የሚያካሂዱትን ተቃውሞ በከለከለ ማግስት ዛሬ በተለይ አዲስ አበባ በተለምዶ ፍልውሃ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ታቅዶ የነበረው ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀረ ። ፖሊስ ከዚሁ መስጊድ ፣ ሶላት ከመጀመሩ በፊት አንድ ምዕመን ከሶላቱ በኋላ ደግሞ ወደ 15 የሚሆኑ ምዕመናን ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ማሰሩን ፣ በአካባቢው እስከነበረበት ጊዜ ድረስ መመልከቱን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግሯል ። ዮሐንስን በስልክ አነጋግረነዋል ።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ