1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫና ዩናይትድ ስቴትስ

ረቡዕ፣ ግንቦት 18 2002

በገዢዉ ፓርቲ ተፅዕኖ ሲደረግበት ነበር።የፀጥታ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ማይክ ሐመር እንደሚሉት ገለልተኛ ወገኖች የምርጫዉን ሒደት እንዳይከታተሉ ታግደዋል፥ ነፃ መገናኛ ዘዴዎችም ጫና ተደርጎባቸዋል

ምርጫዉምስል DW

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉ ምርጫ ዉጤትና ሒደት እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤትና የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ባለሥልጣናት በየፊናቸዉ እንዳሉት የምርጫዉ ሒደት በገዢዉ ፓርቲ ተፅዕኖ ሲደረግበት ነበር።የፀጥታ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ማይክ ሐመር እንደሚሉት ገለልተኛ ወገኖች የምርጫዉን ሒደት እንዳይከታተሉ ታግደዋል፥ ነፃ መገናኛ ዘዴዎችም ጫና ተደርጎባቸዋል።የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጂኒ ኮርሰን በበኩላቸዉ ምርጫዉ አሁን ያለዉን አይነት ዉጤት እንዲኖረዉ ኢትዮጵያ መንግሥት ከአስራ-ስምንት ወራት በፊት ጀምሮ ተፅኖ ሲያደርግ ነበር ይላሉ።ሥለ መግለጫዎቹ ነጋሽ መሐመድ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሮት ነበር።

-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ሥለ ኢትዮጵያ ምርጫ የተነጋሩት ከዲፕሎማሲያዊ ቃላት ባለፍ ሌላ መልዕክት እንደሌለዉ አንድ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂ ተናግረዋል።የምሥራቅ አፍሪቃ የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫዉን አጭበርብሮ ብላ ብታምን እንኳን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ እርምጃ ለመዉሰድ የተዘጋጀች አትመስልም።አቶ ዩሱፍ እንደሚያምኑት ከዋሽንግተን የሚሰማዉ የ«አሳስቦናል መግለጫ»ም የኢትዮጵያ መንግሥትንም ብዙ አያሳስብም።አቶ ዩሱፉን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።

የአሜሪካ ዉጉሚ ሕንፃምስል flickr / NCinDC

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW