1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደትና ቀጣዩ ጉዞ

እሑድ፣ ሰኔ 20 2013

ከኦሮሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዋቂ  የሚባሉት ያልተካፈሉበት የዚህ ምርጫ አሳታፊነት እያጠያየቀ ነው። በትግራይ ምርጫ ባለመካሄዱ የአዲሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋቀቀር ምን ሊሆን እንደሚችልም ማነጋገሩ አልቀረም።«የስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሂደትና የኢትዮጵያ ቀጣዩ ጉዞ »የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።

Parlamentswahl in Äthiopien 2021
ምስል T. Dinssa/DW

የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደትና ቀጣዩ ጉዞ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ የብዙዎችን ትኩረት የሳበውን ስድስተኛውን ብሔራዊና አካባቢያዊ ምርጫ ባለፈው ሰኞ አካሂዳ አጠቃላዩ ውጤት እየተጠበቀ ነው።በዓይነቱ የተለየ በተባለው በሰኔ 15፣2013 ዓ ምኅረቱ ምርጫ ከ40 በላይ ፓርቲዎችና 9500 እጩዎች ተሳትፈዋል።ምርጫን ከታዘቡት አህጉራዊ ድርጅቶች የአፍሪቃ ኅብረት ፣« በስርዓት የተካሄደ ተዓማሚና ሰላማዊ»ሲል የምርጫውን ሂደት አወድሷል። ሌሎች ታዛቢዎችም ከአንዳንድ እንከኖች በስተቀር  የከፋ የሚባል ችግር ያልታየበት ነው ያሉት። ፖሊስም ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ነው የገለጸው።ምርጫው ሰላማዊ ቢሆንም፣የተጠበቁም ያልተጠበቁም ክስተቶችን ማስተናገዱ አልቀረም። በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ዘግይቶ መጀመሩ እና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት፣ በዕለቱ ካጋጠሙ ችግሮች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ምርጫው በማግስቱ የቀጠለባቸው ለጊዜው እንዲቆም  የተደረገባቸው የምርጫ ክልሎችም ከአንድ አምስተኛ በሚበልጡት የምርጫ ክልሎች ምርጫ አልተካሄደም። ከኦሮሞ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዋቂ  የሚባሉት ያልተካፈሉበት የዚህ ምርጫ አሳታፊነት እያጠያየቀ ነው። በትግራይ ምርጫ ባለመካሄዱ የአዲሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋቀቀር ምን ሊሆን እንደሚችልም ማነጋገሩ አልቀረም።«የስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሂደትና የኢትዮጵያ ቀጣዩ ጉዞ »የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።በውይይቱ የሚሳተፉ አራት እንግዶች ጋብዘናል ።እነርሱም ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ የብልጽግና ፓርቲ ቃል አቀባይ፣አቶ ግርማ በቀለ የህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣አቶ ሰሎሞን ተፈራ በአምቦ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም አቶ ደጀን የማነ በወሉ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር ነበሩ።ሆኖም ዶክተር ቢቂላ መጀመሪያ ላይ ከተገኙ በኋላ ስልካቸው ተቋርጦ ልናገናቸው አልቻልንም።የአቶ ደጀን ስልክም አይነሳም። ጥሪያችንን አክብረው ከተገኙልን ከአቶ ግርማ በቀለና አቶ ሰሎሞን ተፈራ ጋር ውይይቱን አካሂደናል ።ሙሉውን ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ምስል M.Teklu/DW

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW