የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና ኦነግ
ዓርብ፣ ጥር 28 2013ማስታወቂያ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መሪዎች የገጠሙትን ዉዝግብ ለማስወገድ ፓርቲዉ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡ ቦርዱ ትናንት ባወጣዉ መግለጫ የግንባሩን ችግር ለመፍታት ከዚሕ ቀደም የተለያዩ አማራጮችን መጠቀምና መጠቆሙን አስታዉቋል። ከእንግዲሕ ግን ቦርዱ የሕግና የአስተዳደር መሳሪዎቹን በመጠቀም ኦነግን የሚያግዝበት መንገድ እንደሌላ አስታዉቋል። በቦርዱ መግለጫ መሠረት የኦሮሞ የነፃነት ግንባርን የመሪነት ሥልጣን ለመያዝ የሚወዛገቡ ኃይላትን ልዩነት ለማስወገድ ግንባሩ ጠቅላላ ጉባኤ ከመጥራት ዉጪ የተረፈዉ አማራጭ የለም።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ