የኢትዮጵያ ምንዛሪ በአፍሪቃ ደካማ ከሆኑት 21 ገንዘቦች መካከል አንዱ ነው ተባለ
ሐሙስ፣ መስከረም 29 2018
በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2025 ከዓለማችን እጅግ ደካማ ገንዘብ ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ 26ኛ ላይ እንደምትገኝ ተዘገበ ። ኢራን ሊባኖስን እና ዚምባብዌን አስከትላ በቀዳሚነት ላይ ትገኛለች ተብሏል ። ከሰሞኑ ይፋ የሆነውን መረጃ ያወጣው XS.com የተሰኘ የምጣኔ ሀብት ተቋም ድረ ገጽ ነው ። በዘገባው መሰረት፦ የኢትዮዸያ ብር ከየመን ቀጥሎ ከሀይቲ ደግሞ የተሻለ በመሆነ በ26 ደረጃ ላይ ሰፍሯል ። የኢትዮጵያ ብር ባለፈው የጎርጎሪዮሱ ዓመትም ከሠሐራ በታች ካሉ ደካማ ገንዘብ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚመደብ የዓለም ባንክ መዘገቡ ይታወሳል ።
የገንዘብ ምንዛሪ ምዘናውን ይፋ ያወጣው የዓለም የምንዛሪ ኤጀንሲ የምንዛሪ ምዘናው የተካሂደው የየሀገራቱ ገንዘቦች ከአሜሪካኑ ዶላር ጋር በሚኖራቸው የምንዛሪ መጠን መሰረት ነው ብሎዋል ።
የብር የመግዛት አቅም መዳከም
ይህ ደግሞ ብር አንድም ጠንካራ ከሆኑት ገንዘቦች ጋር ሲነፃፀር እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለመግዛት በጣም አናሳ የሆነ አቀም ይኖረዋል፥ ሁለትም በሀገር ወሰጥ የተረጋጋ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ እጦት ነፀብራቅ ይሆናል ። በየጊዜው አቅም እያጣ ለመጣው የኢትዮጵያ ብር ማሸቆልቆል በርካታ ምክንያቶች ቤኖሩም የ ኢኮኖሚው አለመረጋጋት በዋነኝነት ተቀምጧል። አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሰት ኢኮኖሚ ለማረጋጋት እና የዋጋ ግሽበቱን ለመቀነስ የተለያዩ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን እየተገበረ ቢሆንም፤ በታሰበለት ልክ የተፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት የቻለ አይመሰልም ።
ባለሞያዎች ምን ይላሉ?
በአዲስ አበባ ዪንቨርሰቲ የፋይናንሰ እና ኢንቨሰትመንት ረዳት ፕሮፊሰር የሆኑት ዶ/ር ሰው አለ አባተ ለዶቼቨሌ እነደገለፁት መንግሰት እያደረገ ያለው የፓሊሲ መሻሻል የብር የመግዛት አቅም ማሸቆልቆልን ለመታደግ ብቻውን በቂ አይደለም ይላሉ ።
መንግሰት የመሪነቱን ሚና ቢጫወትም እንደ ማኅበረስብ ድርሻችንን ካልተወጣን የሀገር ውሰጥ ምርትን ካላሰፋን በሰተቀር ዘላቂ መፈተሄ ሊመጣ አይችልም ሲሉ አክለው ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቀም ለማሳደግ ካልሆነም ባለበት በማረጋጋት እና በዓለም የገንዘብ ገበያዎች ላይ የበለጠ ጠንካራ ለማድረግ ወሳኝ የሆን ርምጃ ከመንግሰትም ከማኅበረሰቡም ካልተወሰደ በስተቀር አሁንም የገንዘብ አለመረጋጋት ማሰወገድ አይቻልም ብለዋል ።
ሐና ደምሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ፀሓይ ጫኔ