1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቃለ መጠይቅ፤ የኢትዮጵያ ሰላም፣ ድርድርና ኦነግ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 18 2016

የድርድሩን ሒደት በቅርብ እናዉቃለን የሚሉ ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን ለድርድሩ መፍረስ በዋናነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ሁለቱ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሳተፈ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት፣ የመንግስት ተቋማት ለዉጥ እንዲደረግባቸዉ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ይገኝባቸዋል።

ዶክተር ሽጉጥ ገለታ የኦነግ ሊቀመንበር የዉጪ ግንኙነት አማካሪ
የኦሮሞ ነፃነት ግንብር ሊቀመንበር የዉጪ ግንኙነት አማካሪ ምስል Privat

ከኦነግ የዉጪ ግንኙነት አማካሪ ከዶክተር ሽጉጥ ገለታ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያ መንግስትና መንግስት ኦነግ/ሸኔ በሚል በአሸባሪነት የፈረጀዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት(ኦነሰ) ተወካዮች ዳሬ ኤስ ሰላም-ታንዛኒያ ዉስጥ ለሁለት ሳምንት ያደረጉት ሁለተኛ ዙር ድርድር ባለፈዉ ሳምንት ያለዉጤት አብቅቷል።ድርድሩ ያለዉጤት ለመበተኑ የሁለቱ ወገኖች ባለስልጣናት አንዳቸዉ ሌላቸዉን እየወቀሱ ነዉ።ይሁንና ከመወቃቀስ ባለፍ በድርድሩ ሒደት የተነሱትን ሐሳቦች፣ ሁለቱ ወገኖች የተስማሙ ወይም የተፋረሱባቸዉን ጉዳዮች ሁለቱም ወገኖች እስካሁን በይፋ አላስታወቁም።ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ መንግስትና የኦነሰ ድርድር ክሽፈት

የድርድሩን ሒደት በቅርብ እናዉቃለን የሚሉ ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን ለድርድሩ መፍረስ በዋናነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ሁለቱ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሳተፈ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት፣ የመንግስት ተቋማት ለዉጥ እንዲደረግባቸዉ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ይገኝባቸዋል።

በሌላ በኩል አንዳድ ታዛቢዎች የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) ከዉጪ በተለይም ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ ተፅዕኖ ይደረግበታል የሚል አስተያየት ይሰጣሉ።በዚሕም ምክንያት ኦነሰ ከመንግስት በኩል የቀረቡለትን ሐሳቦች ለመቀበል መቸገሩን የሚጠቅሱ አሉ።የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር የዉጪ ግንኙነት አማካሪ ዶክተር ሽጉጥ ገለታ ግን ፓርቲያቸዉ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የሚለዉን አስተያየት «በፍፁም« ይላሉ።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ዳዉድ ኢብሳምስል Seyoum Getu/DW

ዶከተር ሽጉጥ እንደሚሉት ለድርድሩ መፍረስ ዋነኛዉ ምክንያት ከገዢዉ ፓርቲ መሰረታዊ ባሕሪ የሚመነጨዉ ሰዎችን በተለይም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን በሥልጣንና በገንዘብ የመደለል ሙከራ ነዉ።ኦነግ በኦሮሚያ ክልል ለኅብረተሰቡ እንግልት መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ

«(ኦነግ) ክሕደትም ስለደረሰብን፣ የአስመራዉ ድርድር በክሕደት ነዉ ያለቀዉ---ሥለዚሕ ዕዉነት ሰላም ፈላጊ ነወይ ይኽ መንግስት? የሚለዉ በጣም ጥርጣሬ አለን---» ይላሉ ዶክተር ሽጉጥ ገለታ።

ዶክተር ሽጉጥ እንደሚሉት ኢትዮጵያን የሚያተራምሰዉን ግጭት፤ ጦርነት፣ እገታና ሁካታ ለማቃለል ሲሆን በመላዉ ኢትዮጵያ ይኽ ቢቀር በኦሮሚያ ሁሉን ያሳተፈ የሽግግር መንግስት መመስረት፣ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ።ከዶክተር ሽጉጥ ጋር ያደረግነዉን ሙሉ ቃለ ምልልስ ያድምጡ።

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW