የኢሶዴፓ ማሳሰቢያ
ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኢሶዴፓ የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነው የዜጎችን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ማስከበር እየተዘነጋ ነው ሲል ወቀሰ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ በሰጡት መግለጫ «መንግሥት ተዘናግቶ ሊቀመጥ አይገባም »«ለችግሩ ትኩረት መስጠት አለበት ብለዋል። በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲሰፍንም ያለ የሌለ ኃይሉን መጠቀም እንደሚኖርበትም ተናግረዋል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ