የኢትዮጵያ ቅርሶች አያያዝና አጠባበቅ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2006ማስታወቂያ
ቀድሞ የተፈጸሙት ተግባራት የሰዎች ስለቅርስ ያላቸዉ እዉቀትና አመለካከት ያስከተለዉ ሊባል ቢችል እንኳ ዛሬም ቅርሶች በተለያየ መንገድ መዉጣታቸዉ በምን ሊመኻኝ ይችል ይሆን? ቅርሶቹ እንዲጠበቁ የየበኩላቸዉን የሚያደርጉ የሀገር ዉስጥም ሆኑ የዉጭ ሃገራት ምሁራን ዛሬም ስለቅርሶቹ ያለዉ ግንዛቤ እንዳልዳበረ ነዉ የሚያመለክቱት። ያሉትም ተመዝግበዉ የሚቀመጡበት ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ በትምህርት ቤት ደረጃም ተገቢዉ ትኩረት ተሰጥቶት ወጣቶች ከልጅነታቸዉ ጀምረዉ ምንነቱን አዉቀዉ እንዲጠበቅ የበኩላቸዉን እንዲያደርጉ የሚመክሩም አሉ። ስለኢትዮጵያ ቅርሶች አያያዝና አጠባበቅ የተጠናቀረዉን ከድምጽ ዘገባዉ ማድመጥ ይቻላል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ