1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አቅም እና ትብብር እስከምን? አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ

ዓርብ፣ መስከረም 23 2018

አምስት የፖለቲካ ድርጅቶችን በማካተተ በቅርቡ የተመሰረተው «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» የተሰኘው ቅንጅት ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ጌጡን አነጋግረናቸዋል። ቅንጅቱን የመሠረቱት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው።

«ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» በሚል ስያሜ በአምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት በይፋ ሲመሰረት
«ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» በሚል ስያሜ በአምስት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅንጅት በይፋ ሲመሰረት፦ ቅንጅቱን የመሠረቱት የፖለቲካ ድርጅቶች የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸውምስል፦ Solomon Muchie/AA

አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ ከ«ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» ሰብሳቢ ጋር

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ  ውስጥ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶችን በማካተተ «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» የተሰኘ ቅንጅት በቅርቡ ተመስርቷል ። የቅንጅቱ ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ጌጡን በስልክ አነጋግረናቸዋል ።  «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» ወይም ባጭሩ «ለኢትዮጵያ» በሚል ስያሜ ቅንጅቱ በይፋ የተመሰረተው ቅዳሜ መስከረም 10 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ነው ። 

አቶ አብርሃም፦ በፕሬዚደንትነት የሚመሩት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን ጨምሮ በአምስት ፓርቲዎች ስለተመሰረተው ቅንጅት ምንነት እና ዓላማው ለዶይቸ ቬለ (DW) አብራርተዋል ። 

ቅንጅቱን የመሠረቱት የፖለቲካ ድርጅቶች የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ናቸው።

ለአቶ አብርሃም ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፦ አምስቱ ፓርቲዎች ለሦስት ዓመት ተኩል በትብብር ስትሠሩ መቆየታችሁ ተገልጧል ።  ቅንጅቱን በአሁኑ ወቅት መመስረት ለምን አስፈለጋችሁ? ምናልባት ለምርጫ ብለው ነው የሚሉ ስላሉ ነው ። 

ለመሆኑ አዲሱ ቅንጅት በ97ቱ ምርጫ ከነበረው ቅንጅት በምን ይለያል?

ከዚህ ቀደም እጅግ በርካቶች ተስፋ ጥለውበት የነበረ ቅንጅት ተመስርቶ መጨረሻው አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ተጠናቅቋል ። አንዳንዶቹም አሁን ካለው መንግሥት ጋር ሥልጣን ተሰጥቷቸው እየሠሩ ነው ።  ከቀደመው ቅንጅት  «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት»  ምን ትምሕርት ወስዳችኋል?

ብዙውን ጊዜ ፓርቲዎች ወይንም ቅንጅቶች የሚፈርሱት ከሕዝቡ ፍላጎት የራሳቸውን ፍላጎት እያስቀደሙ ነው ይባላል ። እናንተ ሕዝቡን ለማስቀደም ምን ያህል ተዘጋጅታችኋል? ብታሸንፉስ የባለፈው ቅንጅት አይነት አሳዛኝ ድርጊት ላለመደገሙ ምን አሳብ አላችሁ? 

ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ ሌሎች የሰላማዊ ትግል ስልቶችን እንደምትከተሉ በቅንጅቱ ምሥረታ ወቅት ዐሳውቃችኋል ። ምን አይነት የሰላማዊ ትግሎችን ለመከተል ዐስባችኋል? እጅግ ጠብቧል በሚባለው የፖለቲካዊ ምሕዳርስ ምን ያህል ልንጓዝ እንችላለን ትላላችሁ? የሚሉት ይገኙበታል ።

«ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» ከተሰኘው ቅንጅት ሰብሳቢ አቶ አአብርሃም ጌጡ ጋር የተደረገው ሙሉ ውይይት ከታች ይገኛል ።

ሙሉ ቃለ መጠይቁን በድምፅ ማእቀፉ በኩል ማዳመጥ ይቻላል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW