1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ተስፋ እና ተግዳሮት

ሥዩም ጌቱ
ማክሰኞ፣ መስከረም 13 2018

በተለይም ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለው ወቅት በኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለጎብኚዎች ለመሸጥ ዋነኛው ወቅት ነው ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት ላይ ወደ አገሪቱ የሚገቡት የጎብኚዎች ቁጥር አገሪቱ በምትመኘው ልክ አለመሆኑን ነው የዘርፉ ሙያተኞች የሚገልጹት፡፡

የክሱም ሐዉልቶች በከፊል።ባለሙያዎች እንደሚሉት የአክሱም ሐዉልቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ነባር የቱሪስት መስሕብ የሚገኙባቸዉ አካባቢዎች በፖለቲካ ቀዉስና ግጭቶች የሚታወኩ በመሆኑ የሐገር ጎብኚዉ ቁጥር እንዲቀንስ አድርጎታል።
የክሱም ሐዉልቶች በከፊል።ባለሙያዎች እንደሚሉት የአክሱም ሐዉልቶችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ነባር የቱሪስት መስሕብ የሚገኙባቸዉ አካባቢዎች በፖለቲካ ቀዉስና ግጭቶች የሚታወኩ በመሆኑ የሐገር ጎብኚዉ ቁጥር እንዲቀንስ አድርጎታል።ምስል፦ Million Haileselasie/DW

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ተስፋ እና ተግዳሮት

This browser does not support the audio element.

               
ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቱሪዝም ዘርፉ ከዋና ዋናዎቹ የክፍለ-ኢኮኖሚው ምሰሶዎች ዝርዝር በመግባቱ ለዘርፉ በርካታ መሰረተ ልማቶች እንደተሰሩለት እየተነገረ ነዉ፡ሆኖም ባለፉት አምስት ዓመታት በተከታታይ በበርካታ የአገሪቱ አከባቢዎች የሚደረገዉ ግጭት ግን  ለዘርፉ ፈተና ሆኖ በመቆየቱ ሊገኝ የታሰበው ገቢ አለመገኘቱም ይጠቀሳል፡፡
አሁን ላይ በተለይም ከመስከረም ወር ጀምሮ ያለው ወቅት በኢትዮጵያ ቱሪዝምን ለጎብኚዎች ለመሸጥ ዋነኛው ወቅት ነው ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት ላይ ወደ አገሪቱ የሚገቡት የጎብኚዎች ቁጥር አገሪቱ በምትመኘው ልክ አለመሆኑን ነው የዘርፉ ሙያተኞች የሚገልጹት፡፡

ዋነኛው የቱሪዝም መዳረሻ ወቅት በኢትዮጵያ 

አቶ ፍስሃ አስረስ በቱሪዝም እና ደህንነቱ ዘርፍ በተለይም በሆቴሎች አገልግሎት ሙያ ላይ በአገር ውስጥ እና ከኢትዮጵያም ውጪ ለዓመታት ሰርተዋል፡፡ ባሁን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የሆቴሎች እና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ አማካሪ ሆነው የሚሰሩት ባለሙያው አሁን የምንገኝበት የመስከረም ወር በዓለም አቀፍም ደረጃ ቱሪዝም በስፋት ትኩረት የሚገኝበት እነደሆነና በኢትዮጵያ ውስት ደግሞ ትልቁ የቱሪስት መስዕብ ወቅት እንደሆነ ያሰምራሉ፡፡ 
“አገራችን ከዘመን መለወጫ ጀምሮ መስቀል እና እሬቻን የመሳሰሉ ተላላቅ የጎብኚዎች መዳረሻ የሚያደርጋት ሁኔቶችን የምታስተናግድበት ወቅት በመሆኑ ከአገር ውጪም ከአገር ውስጥም ጎብኚዎች የምንቀሳቀሱባት ወቅት በመሆኑ ለዚህ የመዳረሻ አገልግሎቶች መኖር ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” በማለትም ከዚህ አኳያ በተለይም መዲናዋ አዲስ አበባን የኮንፌረንስ ቱሪዝም ለማድረግ የተሰራው ስራ ውጤትም ማስገኘት መጀመሩን ይጠቁማሉ፡፡
ከዚህ አኳያ በመዲናዋ አዲስ አበባ ላይ በቅርብ ዓመታት የተሰሩ የመዳረሻ ስራዎች ፍሬ እያፈራ ነው በሚለው ሃሳብ በመስማማት አስተያየቱን የሚሰጠው የቱሪዝም ጋዜጠኛው ሄኖክ ስዩም፤ ተገኝቷል የሚለውንም ውጤት ይጠቁማል፡፡ “አዲስ አበባ አለ ብዬ ማስበው በተለይም ክረምቱን አከባቢ ዓለማቀፍ ስብሰባዎችን በማስተናገድ ላይ የከረመው የኮንፌረንስ ቱሪዝም ዘርፉን ለማስተዋወቅና ለማነቃቃት ባኖረው ሚና አሁን በሳምንቱ መጨረሻ ለምናከብረው የመስቀል በዓል የጎብኚዎች ፍላጎት ከፍ ብሎ እንድንጠብቅ አስችሎናል”ይላልም፡፡ ከዚህ የተነሳ አዲስ አበባ ከዚህ በፊት ከነበረውም በተሻለ መጠን ጎብኚዎችን እንደምታስተናገድ ተስፋ እና ተጨባጭ ፍላጎት መኖሩንም ባለሙያው ጠቁሟል፡፡

ግጭት ያለባቸው አከባቢዎች ለቱሪዝም እንደ ማነቆ

ይሁንና ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ እና ግጭትየሚስተዋልባቸው አከባቢዎች አሁንም የጎብኚዎችን መዳረሻ ፈተና ውስጥ ከቶ እንደዘለቀ ነው፡፡ በተለይም በዚህን ወቅት በጎብኚዎች መዳረሻነት የምታወቁትን ሰመሜናዊውን የአገሪቱን ክፍል የሚስተዋለው የሰላምና መረጋጋት እጦት ለዘርፉ ፈተና ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ሄኖክ እንደምለው፤ “የመስቀል በዓልን በሚገባው ስናስተዋውቅ የኖርነው የሰሜኑን የመስቀል አከባበር ነውና ከዚህ አኳያ የሚፈለገው መጠን ያህል ጎብኚ መጥቷል ወይ የሚለው ጥያቄን የሚፈጥር ነው”፡፡
የሆቴልና ሆስፒታሊቲ አማካሪው አቶ ፍስሃ በፊናቸው አሁንም ድረስ ግጭት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን በመጠቆም፤ እየተሰሩ ያሉ አማራጭ የመዳረሻ ልማቶች ግን በቀጣይአማራጭ ተስፋን የሚስጨብጡ እንደሆነ ነው አስተያየት የሰጡን፡፡ “ካሁን በፊት በማይታወቁም አከባቢዎች የቱሪዝም መዳረሻ ልማቶች እየተሰሩ ነው” በማለትም ይህ የፈጠረው መነቃቃት ሰላምን አብዝቶ ለሚፈልገው የቱሪዝም ዘርፍ ሰላም ለማምጣት ሁሉም ባለድርሻ አካል አተኩሮ ልሰራበት እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡ “ኢትዮጵያ ውስጥ ከግብርናው ቀጥሎ ብዙ የሰው ሃይልን በማስተናገድና የስራ እድል በመስጠት የሚታወቀውን የቱሪዝም ዘርፍ በተያዘው 2018 ዓ.ም. ግጭት በማቆም የአቅሙን ያህል ስራ ላይ ማዋልም ያስፈልጋል” ሲሉ ነው ሃሳባቸውን የቋጩት፡፡

ነቀምት የሚገኘዉ የወለጋ ሙዚየም የአካባቢዉን ጥንታዊ ቅርስና ባሕላዊ እሴቶች ለማሳየት የሚረዱ የቱሪስት መስሕቦች እንዳሉበት ይነገራልምስል፦ Negassa Desalegn/DW

የቱሪዝም ገቢያ ላይ የሚጎላው ድክመት

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ከቱሪዝም ጋር ተያይዞ ያለው ትልቁ ክፍተት የአማራጭ የቱሪዝም ገቢያው ሽያጭ ላይ የሚስተዋል ክፍተት ነው የሚለው የቱሪዝም ጋዜጠኛው ሄኖክ ሥዩም አሁን ላይ በዘርፉ ትልቁን ሽንቁር ያሳየውም ይሄ ነው ይላል፡፡ “እኛ ትልቁ ድክመታችን ፒክ ስዝን በምንለው መስከረም ላይ ደቡባዊ  የአገሪቱ አከባቢዎች ላይ ያሉትን እምቅ የቱሪዝም ሃብቶች፤ ለአብነትም የጉራጌና በሌሎችም አከባቢዎች የሚከበረውን መስቀል አለማስተዋወቅና በሚገባው አለመሸጣችን ነው” የሚለው ሄኖክ ለዓመታት የቱሪዝም አቅጣጫውና የገቢያ ሽያጪ ተመሳሳይ የሆነውን የሰሜን አከባቢዎች ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ መቆየቱ አከባቢው ግጭት ላይ በሆነበት ባሁን ወቅት ዘርፉን ጎድቶት መቆየቱንም አንስቷል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW