የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋጋ ማሻሻያ እና የበደንበኞች ቅሬታ
ዓርብ፣ መስከረም 23 2018
የደንበኞቺ ቁጥር ከ43.1 ሚሊዮን በላይ አድጉዋል የሚለው ንግድ ባንክ የአገሪቱን ግማሽ የሚጠጋ የባንክ ገበያን ከ92 በመቶ በላይ የሚሆነው የገንዘብ ልውውጥ ያካሄዳል .ከ13 ትሪሊየን ብር በላይ የሚገመተው የገንዘብ ልውውጥ በዲጂታል መድረኮች የሚከናውን እንደሆነም የሚናገረው ንግድ ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት ብቻ 1.69 ትሪሊየን ብር መገኘቱን አስታውቋል።
በቅርቡ ንግድ ባንክ በሞባይል እና በዲጂታል የባንክ መድረኮች ለሚካሄዱ ክፍያዎች ያደረገው የክፍያ ማሻሻያ የጨመረው የ አእልግሎት ከፍያ ከፍተኛ ከመሆኑ በላይ ደንበኞቹ አግባብ አለመሆኑን ይናገራሉ ። የዲጂታል ባንኪንግ አካውንት ወደ አካውንት የሚሸጋገርበት ጊዜ ከ ተለመደው የ15 በመቶ ግብር ክፍያ በተጨዋማሪ ባንኩ የሚጠይቀው የአገግሎት ክፍያ ከፍተኛ ነው በተለይ ከንግድ ባንክ ወደሌላ ባንክ የሚደርግ የገንዘብ ሽግግር የአገልግሎት ክፍያ እጅግ ከፍተኛ ነው። .
ለምሳሌ ከንግድ ባክ ወደ አዋሽወይም አቢሲኒያ ባንክ አንድ ሰው 100 ብር ማስተላልፍ ቢፍልግ 15 ከመቶ ታክስ /ግብር 0.80 ሳንቲም ይከፋላል ባንኩ የአገልግሎት ክፍያ በሚል 5፣40 ሳንቲም ይቆርጣል በዚህም አንድ የንግድ ባንክ ደንበኛ ከንግድ ባንክ ወደ አዋሽ ወይም አቢሲኒያ ባንክ ለሚደርገው 100 ብር ሽግግር ብር 106.40 ሳንቲም ለመክፍል ይገደዳል . በተምሳሳይ ከንግድ ባንክ ወደቲሌ ብር ለሚደረግ የ100 ብር የገንዘብ ሽግግር ደግሞ 15 በመቶ ታክስ 1.50 እና 10 .00 ብር የአገልግሎት ክፍያ ንግድ ባንክ ይወስድ እና ከደንበኛውን 111.50 ይቆርጣል ማለት ነው።.
በሌላ በኩል በተመሳሳይከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ወደ ንግድ ባንክለሚደረግ የመቶ ብር ዝወወር ግብር 0.09 ሳንቲም የአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 0.60 ሳንቲም በአጠቃላይ 0.69 ሳንቲም ያሥከፍል እና 100.69 ሳንቲም ከደንበኛው ላይ ይቆርጣል ማለት ነው የህም በ 5.71 ሳንቲም ከንግድ ባንክ ጋር ልዪነት አለው ማለት ነው። ከአዋሽ ባንክ ወደ ቲሌ ብር የሚደረግ ተምሳሳይ የመቶ ብር ሽግግር ደግሞ ግብር 0.30 ሳንቲም የአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 2፣00 ብር በአጠቃላይ 102.30 ሳንቲም ይሆናል ይህም ንግድ ባንክ ከሚያስከፍለው 111.50 ጋር ሲነፃፀር የ ብር 9፣20 ሳንቲም ልዪነት አለው ማለት ነው። .በታማኝነት ከ ባንኩ ጋር የቆዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ጭማሪው አላግባብ ከመሆኑም ባሻገር ያለብንን የኑሮ ጫና በጭራሽ ያላገናዘበ ነው ሲሉ ዶቼቪሌ ተናገረዋል። ባንኩ የደንበኞቹን ቅሪታ ሰምቶ በጥናት የተደገፍ ምላሽ መስጠት ካልቻለ በደንበኞቹ ዘንድ ታማኝነት ሊያሳጣው እንደሚችልም የባንኩ ተገልጋዪች ተናግረዋል ።
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጥነው ያድምጡ።
ሀና ደምሴ
ነጋሽ መሀመድ
ፀሐይ ጫኔ