1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት ምን ይጠበቃል? አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ

ዓርብ፣ ጥር 23 2017

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ የአገራቸውን ስም በዓለም መድረክ ያስጠሩ በርካታ ብቃት ያላቸውን አትሌቶች ፌዴሬሽኑ የማፍራቱን ያህል በተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችም ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል ። ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት አትሌት ስለሺ ሥኅን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ። ሙሉ ቃለ መጠይቁን በድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።

Sileshi Sehen EAF
ምስል፦ EAF

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

This browser does not support the audio element.

በቅርቡ  የኢትዮጵያ  አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዚደንት መርጧል ። የአገራቸውን ስም በዓለም መድረክ ያስጠሩ በርካታ ብቃት ያላቸውን አትሌቶች ፌዴሬሽኑ የማፍራቱን ያህል በተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችም ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል ።

አትሌቶችን በዓለም አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪ እንዲሆኑ በመምረጥ ሒደት አድልዎ ይፈጸማል፤ በኦሎምፒክ ውድድሮች ወቅትም ተደጋጋሚ በደሎች ይደጋገማሉ የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ ። ይህን እና ሌሎች የፌዴሬሽኑን ስሞች በበጎም ሆነ በመጥፎ የሚያስነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአዲሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አትሌት ስለሺ ሥኅን ጋር ማንተጋፍቶት ስለሺ ቀጣዩን ቃለ መጠይቅ አድርጓል ። 

አትሌት ስለሺ ሥኅን፦ በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር በ2004 በአቴንስ እንዲሁም በ2008 በቤጂንግ  ኦሎምፒክ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ነው ። በዓለም ሻምፒዮና ለሦስት ጊዜያት የብር አንድ ጊዜ የነሐስ ሜዳሊያ ካገኛቸው ድንቅ ድሎች የሚጠቀሱለት ናቸው ። አትሌት ስለሺ ሥኅን በሦስት ሺህ፣ በአምስት ሺህ እንዲሁም በዐሥር ሺህ ሜትር በዓለም አቀፍ መድረኮችም ይታወቃል ።

ሙሉ ቃለ መጠይቁን እንድታደምጡ እንጋብዛለን ። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW