የኢትዮጵያ አትሌቶች ማጣሪያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2008ማስታወቂያ
በሪዮ ደጀኔሮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ርቀቶች የሚወዳደሩ አትሌቶች ምርጫ እየተካሄደ ነው ። ኢትዮጵያውያን ውጤታማ በሆኑበት በ10 ሺህ ሜትር ርቀት በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ማንነት ዛሬ ምሽት በኔዘርላንድስ ሄንግሎ ከተማ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ይለያል ። በርካታ ወጣት እና ታዋቂ አትሌቶች በሚሳተፉበት በዛሬው ውድድር በቅርቡ በሪዮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን ከሚወከለው ቡድን ውጭ የሆነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ይካፈላል ። ቀነኒሳ ዛሬ በጥሩ ሰዓት ውድድሩን ከጨረሰ በሪዮው ኦሎምፒክ በማራቶን ለመካፈል ያጣውን እድል በ10 ሺህ ሜትር ያሳካል ተብሎ ይጠበቃል ። ከሴቶች አትሌት መሠረት ደፋር ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም ከውድድር ውጭ መሆንዋ ተገልጿል ። የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ አላት ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ