1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በርካታ በረራዎች ያስረዘው የትናንቱ የአየር ሁኔታ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 18 2016

በትናንትናው እለት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ከሰዓት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ 42 በረራዎች መስተጓጎል ማጋጠሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ በትናንት ጠዋቱ የአየር ሁኔታ ሊያደርግ የነበረውን ሁሉንም በረራ በመሰረዙ ፤ከመንገደኞች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብቶ ነበር።

አየር መንገዱን በዚህ መጠን የከፋ የአየር ጠባይ አጋጥሞ አያውቅም
የአየር መንገገዱ የህዝብ ግንኙነትና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሀና አጥናፉ እንደገለፁት አየር መንገዱን በዚህ መጠን የተፈታተነ መሰል የከፋ የአየር ጠባይ አጋጥሞ የማያውቅ መሆኑም ተገልጿል፡ምስል AP

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጋጠመው መጥፎ የአየር ሁኔታ እና የመንገደኞች አምቧጋሮ

This browser does not support the audio element.


በትናንትናው እለት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ከሰዓት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ 42 በረራዎች መስተጓጎላቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ በትናንት ጠዋቱ የአየር ሁኔታ ሊያደርግ የነበረውን ሁሉንም በረራ መሰረዙንም አስታውቋል፡፡
የአየር መንገገዱ የህዝብ ግንኙነትና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሀና አጥናፉ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት አየር መንገዱ በትናንትነው እለት የተስተስተጓጎሉ በረራዎችን በማስተካከል ስራ ተጠምዶ አምሽቶ ውሏልም፡፡አየር መንገዱን በዚህ መጠን የተፈታተነ መሰል የከፋ የአየር ጠባይ አጋጥሞ የማያውቅ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ትናንት ማምሻውን አየር መንገዱ ወደ መቀለ ሊደርግ የነበረውን በረራ በመሰረዙ በአውሮፕላኑ ውስጥ “ከልክ ያለፈ አምቧጋሮ አንስተዋል” የተባሉት በህግ ሊጠየቁ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

ትናንት ማምሻውን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ልደረግ የነበረው የአገር ውስጥ በረራ በመቀለ አከባቢ ተፈጥሯል በተባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ አንደኛው በረራ እንዲሰረዝ በአየር መንገዱ ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ ከተሳፋሪዎች አንዱ አጉልተው ያስነሱት ተቃውሞና ቅሬታ የማህበራዊ መገኛኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ነበር፡፡ በርካቶች በቁጣ ምላሽ የሰጡት ድርጊቱ አንድ የአየር መንገዱ ደንበኛ በበረራው መሰረዝ ከአየርመንገዱ ሰራተኞች እና የፀጥታ ሰዎች ጋር የሰላ እሰጣገባ ውስጥ ስገቡ ታይቷል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የህዝብ ግንኙነትና ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሀና አጥናፉ ዛሬ አመሻሹን ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በትናንትናው እለት ያጋጠመው ለበረራ ያልተመቸ የአየር ጠባይ ተከትሎ የተሰረዙ በረራዎች ቀዳሚ የአየር መንገዱ ትኩረት የደንበኞችን ደህንነት የመጠበቅ ግንባር ቀደም መርህ ለመከተል ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በረራዎች በመሰረዛቸው ከመንገደኞች ጋር እሰጣ ገባ ገብቶ ነበር።ምስል Seyoum Getu/DW

የህዝብ ግንኑኘት ኃላፊዋ “አውሮፕላን እንዲበር የሚደረገው ደህንነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡ ትናንት ማምሻውን ወደ መቀሌ ልደረግ የነበረው በረራ ላይ የተወሰደም ይሄው ነው፡፡ ማምሻውን ወደዚያ እንዲበሩ ከተመደቡ ሶስት አውሮፕላኖች ሁለቱ ተነስተው በመቀለ ያለው የአየር ጠባይ ምቹ ባለመሆኑ ተመልሰዋል፡፡ እናም አምብጋሮ የተነሳበት ሶስተኛው በረራ ግን እንዲሰረዝ በመደረጉ ነው ጢቂት ተሳፋሪዎች አምቧጋሮውን ያስነሱት፡፡ አየር መንገዱ ከአስብራሪዎች ጀምሮ መሳወቅ ያለበት ደረጃ ሁሉ ከሄደ በኋላ ነው በጸጥታ ሃይል እንዲወርዱ የተደረገው” ብለዋል፡፡

ትናት ያጋጠመውን የደንበኞች አምቧጋሮ ወደ ህግ ሊወሰድ የሚችል መሆኑንም አየር መንገዱ ጠቁሟል፡፡ “ትናት ከደንበኞቹ የተወሰኑት አንወርድም በሚል አምቧጋሩ ያስነሱት ከበድ ያለ ጥፋት ነው አይደለምየሚለው በህግ ክፍላችን እየታዬ ስለሆኑ ከበድ ወዳሉት ጥፋቶች ጎሮ ከገባ በህግ የሚጠየቁ ሆናል” ሲሉ ነው የጠቆሙት፡፡

በትናንትናው እለት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ከሰዓት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ 42 በረራዎች ተዘርዘዋል።ምስል Seyoum Getu/DW

በትናንትናው እለት አዲስ አበባ ውስጥ ያጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ጠባይ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ብቻ 42 ገደማ በረራዎችን ማስተጓጎሉም ተነግሯል፡፡ “አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ላይ የትናንትናው አይነት የአየር ሁኔታ አጋጥሞን አያውቅም፡፡ ወደ 42 በረራዎችን አስተጓጉሎብናል” ያሉት የአየር መንገዱ የህዝብ ግንኙነትና የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ወደ መዲናዋ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች በሙሉ ወደ ሌሎች የአገር ውስጥ መዳረሻና ሌሎች አገራት እንዲበሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ ደንበኞችን ባቀደው ጊዜ አለማስተናገዱና በመጉላላቱ የሚፈጠር የጊዜ እና ንብረት ብክነት እንደ ክሳራ የሚተመንም ነው ተብሏል፡፡ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ማምሻውን ሌሉትንም በረራዎች መደረጋቸውን፤ ዛሬንም ጨምሮ በረራቸው ተስተጓጉሎ የነበሩ ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝም አየር መንገዱ ተጠምዶ መዋሉም ተጠቁሟል፡፡

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ሥዩም ጌቱ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር  

ፀሀይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW