1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርትና አገልግሎት

ዓርብ፣ መስከረም 22 2013

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ እንዳሉት ኩባንያቸዉ በኢትዮጵያዉያን መሐንዲሶች የሚሰሩ ሌሎች የአዉሮፕላን አካላትንም ለአዉሮፕላን አምራች ኩባንዮች ለመሸጥ አቅዷል

Äthiopien Seattle Boeing Field King County International Airport | Ethiopian Airlines Being 737 Max
ምስል picture-alliance/AP Photo/P. Fiedler

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርት፣ አገልግሎትና ገቢ

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአዉሮፕላን መሥሪያ የሚያገለግሉ የኤሌክትሪክ ገመዶችን (Cabels) እያመረተ ለዩናይትድ ስቴትሱ አዉሮፕላን አምራች ኩባንያ ለቦይንድ መሸጥ መጀመሩን አስታወቀ። የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ እንዳሉት ኩባንያቸዉ በኢትዮጵያዉያን መሐንዲሶች የሚሰሩ ሌሎች የአውሮፕላን አካላትንም ለአዉሮፕላን አምራች ኩባንዮች ለመሸጥ አቅዷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትና ምርቱ እየሰፋ፣ ገቢውም እያደገ መምጣቱን ቃል አቀባዩ አክለዉ ገልፀዋል። ይሁንና የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በያዝነዉ ሳምንት እንደዘገበዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ተሕዋሲ ምክንያት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አጥቷል። 850 ሠራተኞቹ ደግሞ በተሕዋሲዉ ተይዘዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW