የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራሩ
ሰኞ፣ መስከረም 22 2010ማስታወቂያ
ከአሁን በኋላ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና፤ የበረራ፤ የንግድ የፋይናንስ፤ የሰው ሐይል አስተዳደር፤ የደንበኞች አገልግሎት የግዢ አቅርቦት ሥራዎች በሙሉ በኤሌክትሮኒክ የሚከወኑ ይሆናል። አቶ ተወልደ እንደተናገሩት ባለፉት አምስት አመታት ኩባንያቸው የአሰራር ሽግግር ለማድረግ በኢንፎርሜሽን ኮምዩንኬሽን ቴክኖሎጂው ዘርፍ የ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን ገልጠዋል። ሽግግሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በወጪ ቁጠባ እና የአሰራር ቅልጥፍናን በማሳደግ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሏል። ካሁን በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የጉዞ ቲኬቶቻቸውን በድረ-ገፅ መቁረጥ ይችላሉ። አየር መንገዱ ደንበኞቹ በተንቀሳቃሽ ስልክ በሚቀርበው የባንክ አገልግሎት አማካኝነት ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ዳሸን ባንክ እና ኅብረት ባንክ ጋር ሥምምነት ፈፅሟል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ