የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ ጀመረ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 19 2015![Äthiopien Der erste Flieger landete regionalen](https://static.dw.com/image/64230646_800.webp)
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ወራት በኃላ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እንዲሁም ከመቐሌ ወደ አዲስ አበባ መደበኛ የመንገደኞች የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት ጀመረ። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ መቐለ ደርሷል ። አልፎ አልፎ የሚደረግ የረድኤት ድርጅቶች በረራ ከማስተናገድ በስተቀር ከስራ ውጭ ሆኖ የቆየው የመቐለው አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ዛሬ 138 ተጓዦች የጫነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ተቀብሏል። አውሮፕላኑ ከመቀሌ መንገደኞችን ጭኖ ወደ አዲስ አበባም ተመልሷል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የሰላም ስምምነት በተፈራረሙ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተጀመረው በረራ በጦርነቱ ምክንያት የተለያዩ ቤተሰቦችን አገናኝቷል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው መንገደኞች በአገልግሎቱ መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የበረራዎቹ ቁጥር እንዲጨምርም ጠይቀዋል።ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ