1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 125 አዳዲስ አውሮፕላኖች ሊገዛ ነው

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2016

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። አየር መንገዱ ገቢውን ያገኘው በዋናነት ካጓጓዛቸው 17.1 ሚሊዮን መንገደኞች እንዲሁም ከጭነት አገልግሎት ነው። አየር መንገዱ እስከ 2030 ድረስ የሚረከባቸው 125 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙም ተገልጿል።

Äthiopien führt Währungsabwertung ein
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትርፋማ አመት ማሳለፉን አስታወቀ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዕድገት ላይ 

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መሥፍን ጣሰው ዛሬ ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ አየር መንገዱ ይህንን ገቢ ያገኘው በዋናነት ካጓጓዛቸው 17.1 ሚሊዮን መንገደኞች እንዲሁም ከጭነት አገልግሎት ነው። አየር መንገዱ እስከ 2030 ድረስ የሚረከባቸው 125 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙም ተገልጿል።

በቶጎ፣ ማላዊ እና ዛምቢያ አየር መንገዶች ድርሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖቹን ወታደሮችን ለማመላለስ ይጠቀምበታል ለሚለው እንዲሁም፣ የኤርትራ አቬሽን ባለስልጣን ሰሞኑን በአየር መንገዱ ላይ በወሰደው እርምጃ ዙሪያ ለቀረቡ ጥያቄም ምላሽ ሰጥቷል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት 16 አውሮፕላኖችን ለማስገባት እና የተጓዦችን ቁጥር ወደ 20 ሚሊየን ለማሳደግ ውጥን መያዙ ተነግሯል። ዓመቱ ለአየር መንገዱ "የዕድገት ዓመት" እንደነበርም ተገልጿል።ምስል Solomon Muchie/DW

የኤርትራ መንግሥት የበረራ አገልግሎት እግድና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት 16 አውሮፕላኖችን ለማስገባት እና የተጓዦችን ቁጥር ወደ 20 ሚሊየን ለማሳደግ ውጥን መያዙ ተነግሯል። ዓመቱ ለአየር መንገዱ "የዕድገት ዓመት" እንደነበርም ተገልጿል።

ሰሞኑን የሶማሌ ዜግነት ያላት መንገደኛ በአየር መንገዱ ያለአግባብ ተጉላላች በሚል የተለቀወው ምስል የተሳሳተ ነው ያሉት ዋና ሥራ አሥፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው "ትክክለኛ ክስ አይደለም"፣ አንቀበለውም ብለዋል። የኤርትራ አቪየሽን ስለወሰደው ሰሞነኛ የእግድ እርምጃም ተጠይቀው "ይህንን ውሳኔያቸውን እንደገና ያዩታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ግዢ

የአውሮፕላን መለዋወጫ እቃዎች እና የአውሮፕላን እጥረት በአየር መንገዱ ሥራ ላይ ጫና መፍጠራቸውን የገለፁት አቶ መስፍን፣ የነዳጅ እጥረት አለም ላይ ያሉ ጦርነቶች፣ ከአንዳንድ ሀገራት የአየር ክልል ፈቃድ አለማግኘት ወይም ከፍተኛ ግብር መጠየቅ የገጠሟቸው ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አየር መንገዱ ምን ያህል አለም አቀፍ የአቪየሽን ሕጎችን አክብሮ ይሥራል ለሚለው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል።

የአውሮፕላን መለዋወጫ እቃዎች እና የአውሮፕላን እጥረት በአየር መንገዱ ሥራ ላይ ጫና መፍጠራቸውን የገለፁት አቶ መስፍን፣ የነዳጅ እጥረት አለም ላይ ያሉ ጦርነቶች፣ ከአንዳንድ ሀገራት የአየር ክልል ፈቃድ አለማግኘት ነው ብለዋል።ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ነቀምቴ የጀመረው በረራ

"ላረጋግጥላችሁ የምወደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ አሠራሮችን ተከትሎ የሚሠራ መሥሪያ ቤት ነው"

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወታደሮችን ሲያጓጉዝ ይታያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚል ጥያቄ ከዶቼ ቬለ የቀረበላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲህ ያለው አሰራር መኖሩን ጠቅሰው አገልግሎቱ በተለይ ለተባበሩት መንግሥታት የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል። ይህንን በተመለከተ "አውሮፓዊያን ጠይቀውን አውሮፕላኖችን ፋይናንስ አናደርግላችሁም ብለውን ይህንን አስረድተን አሠራራችን ከአለም አቀፍ አሠራር ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ አውሮፕላኖቻችንን እንድናመጣ አድርገዋል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

"አውሮፓዊያን ጠይቀውን አውሮፕላኖችን ፋይናንስ አናደርግላችሁም ብለውን ይህንን አስረድተን አሠራራችን ከአለም አቀፍ አሠራር ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ አውሮፕላኖቻችንን እንድናመጣ አድርገዋል" ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማስፋፊያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "የሰላም አምባሳደር ሆኖ ይቀጥላል እንጂ ግጭት ውስጥ አይሳተፍም" ያሉት ዋና ሥራ እስፈፃሚው አየር መንገዱ የማስተዳደር ኃላፊነትን ጨምሮ በቶጎ አየር መንገድ 26፣ በማላዊ አየር መንገድ ደግሞ 49 በመቶ ድርሻ እንዳለው እንዲሁም በዛምቢያ አየር መንገድ 46 በመቶ ድርሻ ያለው መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ1500 በላይ ፓይለቶች፣ 139 አውሮፕላኖች እንዲሁም 209 መዳረሻዎች እንዳሉትም በዛሬው መግለጫው ተጠቅሷል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW