1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮጳ ኢትዮጵያ የኢንቬስትመንት መድረክ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2018

ሰሞኑ ፓሪስ በተካሄደው የአውሮፓ ኢትዮጵያ የኢንቬስትመንት መድረክ ላይ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስራ ግንባታን ለመደገፍ ና በስራውም ለመሳተፍ ኤርባስና ሌሎችም የአውሮጳ ኩባንያዎች ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ታውቋል። ከቦይንግ ጋር የዘለቀው የኢትዮያ አየር መንገድ የንግድ ትስስር አሁን ከኤርባስ ጋር እየተጠናከረ እንደሚሄድ ይጠበቃል።

Mesfin Tassew, Vorstandsvorsitzender von Ethiopian Airlines
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አየርመንገድ በአውሮጳ ኢትዮጵያ የኢንቬስትመንት መድረክ

This browser does not support the audio element.

የ75 ዓመት ስኬታማ ጉዞ ባለቤትየኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ እንደሚያስገነባው የሚጠበቀው አዲሱ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አስራ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ሊያስወጣው እንደሚችል ተነግሯል። ፕሮጀክቱ የአየር መንገዱ ታላቅ እምረታ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃን የአየር ትራንስፖርት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው የሚጠበቅ  ነው ተብሏል። 
ከአፍሪቃ ልማት ባንክ ባሻገር አሜሪካም ፕሮጀክቱን በገንዘብ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች።

ሰሞኑን  በፓሪስ ከተማ በተካሄደው የአውሮፓ ኢትዮጵያ የኢንቬስትመንት መድረክ ላይም ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስራ ግንባታን ለመደገፍና በስራው ላይም ለመሳተፍ ኤርባስና ሌሎችም የአውሮጳ ኩባንያዎች ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ታውቋል። ይህም ረዥም ዓመታትን በንግድ ትስስር ከቦይንግ ጋር የዘለቀው የኢትዮያ አየር መንገድ አሁን ከኤርባስ ጋር እየተጠናከረ እንደሚሄድ ይጠበቃል። የንግድ ግንኙነትን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የገበያ ፉክክር በምን መልኩ ሊያስተናግደው ይችል ይሆን ?

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ 


 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW