1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ጀመረ

ዓርብ፣ መጋቢት 16 2014

ሁሉም ኢትዮጵያ ለብሔራዊ ምክክር እንዲዘጋጅ ጥሪ ቀረበ። የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ  ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ዛሬ ኮሚሽኑ በይፋ ስራውን መጀመሩን ባሳወቀበት ስነ ስርዓት ላይ  ባሰሙት ንግግር የትምህርት ደረጃ እድሜና ጾታ ሳይለይ ሁሉም ኢትዮጵያ ለብሔራዊ ምክክር እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

Äthiopien | National Consultative Commission
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ጀመረ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዛሬ ልዩ ልዩ የሃይማኖት ተቋማት የፀሎት ሥነ ሥርዓት እንዲያደርጉ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ደግሞ የሰላም መልእክት እንዲያስተላልፉ በማድረግ ሥራውን ጀምራል። የሃይማኖት መሪ አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም፣ መረጋጋት እና እርቅ እንዲሰፍን ተመኝተዋል።
በአዋጅ ቁጥር 1265/ 2014 ዓ.ም የተቋቋመው ይህ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሕዝብ ከተጠቆሙ 632 ሰዎች መካክል 11 ሰዎችን በኮሚሽነርነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤ መሾማቸው ይታወሳል።
የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዛሬው የፀሎት ሥነ ሥርዓት ላይ የአገር ሽማግሌዎች ለብዙ ዓመታት ተሰሚነት እንዳይኖራቸው የተደከመበት ቢሆንም ኢትዮጵያን ክብዙ መከራና ጥፋት እንደታደጉ ምስክሮች ነን፣ የሀገር ሽማግሎዎች ተሰምተው ቢሆን ኖሮ የሰሜን ኢትዮጵያው ችግር ባልደረሰ ነበር ብለዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን አክለውም ከደቂቅ እስከ ልሂቅ ፣ ወጣት ፣ አዛውንት፣ ሴት ወንድ ሳይል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለብሔራዊ ምክክር እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል። ኮሚሽኑ የተጣለበትን ከፍተኛ አገራዊ ሃላፊነት እንዲያሳካ ይህ ያስፈልጋል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ሥራ ማመቻቸት ሲሆን ዋናው ተግባርና ውሳኔ ግን የሕዝብ መሆኑ ሊታወቅ ይገበልም በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኢትዮጵያ ውስጥ በልሂቃን መካከል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ ፣ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዴሞክራሲ የሽግግር ሂደቱን ፈታኝ በማድረጉ ማስፈለጉ መገለፁ ይታወሳል። 
ኮሚሽኑ መሰረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶች ምክንያቶችን በመለየት ገለልተኛ ናቸው ተብለው በተሾሙት 11 ሰዎች እየተመራ ጉዳዮቹ ላይ ውይይት እንዲካሄድባቸው ያደርጋል።በዚህም መተማመን የሰፈነበት አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት ለመፍጠር ይሰራል በሚል ውጥን ተይዞ መቃቋሙ ይታወሳል።
ሶሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 
 

ምስል Solomon Muchie/DW
ምስል Solomon Muchie/DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW