1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
እምነት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መግለጫ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2013

ሕዝብ ሙስሊሙ የኢድ በዓል ሲያከብር በመተባበርና በሰላም መሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ። አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ሁለተኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል ሐሙስ እንደሚከበርም ዛሬ ከመስቀል አደባባይ መነገሩን አዲስ አበባው ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል ።

Äthiopien Haji Umer Idris
ምስል፦ DW/S. Muchie

ስለመተባበር እና ሰላም ሰብከዋል

This browser does not support the audio element.

ሕዝብ ሙስሊሙ የኢድ በዓል ሲያከብር በመተባበርና በሰላም መሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ። አንድ ሺህ አራት መቶ አርባ ሁለተኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል አከባበር እና ሃይማኖታዊ አንድምታውን በማስመልከት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሃጂ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ለህዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ሃጂ ሙፍቲ በዘንድሮ በዓል ሕዝበ ሙስሊሙ የሚጠበቅበትን አንድነትና ሰላማዊ ተግባራቱን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ሁኔታ ፈተኛ መሆኑንም በመጠቆም፤ ፈተናውን ከውስጥም ከውጭም አንድነት በመፍጠር በመተባበር ዜጎች እንዲፈቱት ጥሪ አቅርበዋል። በዓሉ ሐሙስ እንደሚከበር ዛሬ ከመስቀል አደባባይ መነገሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሥዩም ጌቱ ከስፍራው ዘግቧል።
ሥዩም ጌቱ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW