1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ኔታንያሁ፣ ማክሮ እና ዐቢይ "የእንኳን ደስ አለዎ" መልዕክት ለዶናልድ ትራምፕ አስተላለፉ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ለመመረጥ ለተቃረቡት ዶናልድ ትራምፕ "የእንኳን ደስ አለዎ" መልዕክት አስተላለፉ።

ዶናልድ ትራምፕ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ለመመረጥ ለተቃረቡት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ። ምስል Chip Somodevilla/Getty Images

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የአሜሪካ 47ኛ ፕሬዝደንት ሆነው ለመመረጥ ለተቃረቡት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ። 

የአሜሪካው ወግ አጥባቂ የቴሌቭዥን ጣቢያ ፎክስ ኒውስ ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ጥቅምት 26 ቀን 2017 በተካሔደው ምርጫ የዴሞክራቲክ ዕጩዋን ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሐሪስ አሸንፈዋል በማለት አውጇል።

ይሁንና ሌሎች የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እና አሶሼትድ ፕሬስ ወግ አጥባቂው ፎክስ ኒውስ ከደረሰበት ድምዳሜ ላይ አልደረሱም። 

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት በማስተላለፍ ከቀዳሚዎቹ መሪዎች ጎራ ተቀላቅለዋል። 

ዐቢይ በኤክስ "በእርስዎ የሥልጣን ዘመን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት እጠብቃለሁ" የሚል መልዕክት አስፍረዋል። 

የምርጫውን ውጤት በዐይነ ቁራኛ ከሚጠባበቁ የዓለም መሪዎች አንዱ የሆኑት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በኤክስ ባሰፈሩት መልዕክት ለዶናልድ ትራምፕ "እንኳን ደስ አለዎ" ብለዋል። 

ኔታንያሁ የዶናልድ ትራምፕን ወደ ዋይት ሐውስ መመለስ "ታሪካዊ" ብለውታል። የትራምፕ ፕሬዝደንት ሆኖ መመረጥ "በእስራኤል እና በአሜሪካ መካከል ላለው ታላቅ ትብብር ጠንካራ ቃል ኪዳን ማደሻ" እንደሚሆንም ገልጸዋል። 

የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ በበኩላቸው በተመሣሣይ በኤክስ ባሰፈሩት መልዕክት "ከአራት ዓመታት በፊት እንዳደረግንው በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ነኝ" የሚል መልዕክት ለትራምፕ አስተላልፈዋል። 

ማክሮ ይኸ የሚሆነው "በእርስዎ እና በእኔ እምነት፤ በአክብሮት እና በፍላጎት፤ ለበለጠ ሰላም እና ብልጽግና እንደሚሆን ጽፈዋል። 

ዐቢይ፣ ኔታንያሁ እና ማክሮ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ያስተላለፉት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ሐውስ የሚመልሳቸውን 270 ኤሌክቶራል ኮሌጅ ድምጾች ለማግኘት በተቃረቡበት ወቅት ነው። 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW