የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ቀጣይ ግንኙነት እንዴት?
ሰኞ፣ ነሐሴ 14 2010![Äthiopien Eritrea eröffnet Botschaft beim einstigen Kriegsgegner](https://static.dw.com/image/44695324_800.webp)
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለዓመታት ጥርጣሬ እና ሥጋት የተጫነው ግንኙነታቸውን ለማደስ በቆረጡ በጥቂት ሳምንታት ልዩነት በአፍሪቃ ቀንድ ቀጣና የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በፍጥነት ይቀየር ይዟል። የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ወደ አስመራ ጎራ እያሉ በሁለትዮሽ እና የቀጣናው ፖለቲካ ላይ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እየተመካከሩ ነው። መንገዱን የከፈተው ከረዥም አመታት ማመንታት በኋላ ኢሕአዴግ የአልጀርስ ውሳኔን ለመቀበል ያሳለፈው ውሳኔ ቢሆንም የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን የመሳሰሉ አገራት ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል። እስካሁን በፖለቲከኞች የሚቀነቀነው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወዳጅነት እንዴት ይዘልቃል? የኢትዮጵያ እና የኤርራን ግንኙነት ቀረብ ብለው ያጠኑት ዶክተር ተከስተ ነጋሽን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ አነጋግሯቸዋል።
ገበያው ንጉሤ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሀመድ