የኢትዮጵያ እና ጀርመን ግንኙነት
ዓርብ፣ ጥቅምት 23 2011በጎርጎረሳዉያኑ የካቲት ወር 1908 ዓ.ም የጀርመኑ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤያቸዉን አዲስ አበባ ላይ ለአጼ-ምኒሊክ ቤተ-መንግሥት ሲያቀርቡ ንጉሰ ነገስቱ ታመዉ ነበር። ወቅቱ ሕመማቸዉ ለማገገም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ወርደዉ የተመለሱበት ወቅት እንደነበር ተመልክቶአል። በዝያኑ እለት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት ተወካይ ሆፍማን ፊሊፕን ንጉሱ ተቀብለዉ እንዳነጋገርዋቸዉ የታሪክ ማኅደር ይጠቁማል። ግርማ ሞገሳቸዉ ጽናት እና ትህትናቸዉ እንዲሁም በንግሥና ዘመናቸዉ ፊታቸዉ ላይ ሁሌም ይታይ የነበረዉ ገጽታቸዉ በዝያን ጊዜ ደብዝዞ እንደነበር ሁሉ ይነገራል። ሚኒሊክ እንደታመሙ የጀርመን እና የኢትዮጵያ የወዳጅነት ግንኙነት ሻክሮ አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበርም አንዳንድ የጥናት ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ልጅ እያሱ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አሸናፊ ሆነዉ ብቅ ሲሉ የጀርመኖች ሚና በቤተ -መንግሥት ዉስጥ እንደገና ቦግ እንዳለ ነዉ የተመለከተዉ። የጀርመኖች እና የኢትዮጵያዉያን ግንኙነት መቼ ተጀመረ? እንዴትስ ዘለቀ? ለሚለዉ ጥያቄ ታታሪክ ጸሐፊውን ልዑል ዶክተር አስፋ ወሰን አሥራተ ካሣን ጠይቀናል። የበርሊኑ ወኪላችን የሁለቱን ሃገራት የቆየ እና አሁን ሊቀጥል ሰለሚችለው ግንኙነትም ጠይቆአቸዋል። ሙሉ ቃለ-መጠይቁን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
አዜብ ታደሰ