የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መልስና ማስጠንቀቅያ
ሐሙስ፣ ጥር 25 2015
መንግሥት ኃላፊነቱን በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና በማስከበር ኃላፊነቱን የማይወጣ ከሆነ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ፤ በማካሄድ ችግሩ እንዲፈታ እንደምታደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አስጠነቀቀች። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀናት በፊት ለካቢኔ አባሎቻቸው በሰጡትን ማብራሪያ ቤተ ክርስትያኗን በተመለከተ የሰጡትን ማብራሪያን በብርቱ ተቃውመዋለች።
"በሕገ ወጥ መንገድ ተሹመናል የሚሉት አካላት” በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወዳልተፈቀደላቸው የአገልግሎት ቦታዎች በመግባት በቤተክርስቲያኗ ላይ “ሁከት እየተፈጠረ መሆኑን ለመረዳት ችለናል” ያለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የካቢኔ አባላቶቻቸው በዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዳያስገቡ ማዘዛቸው “መንግሥት ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን ችላ ያለበት ነው” በማለት ተችታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ ከቤተ ክርስትያኗ ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀኃፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ይህንኑ በተመለከተ ለሕዝብ የተነበበው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቤተ ክርስትያኗ የገጠማትን ፈተና አቅልለው አይተዋል፣ በቤተ ክርስትያኗ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል፣ ማብራሪያቸው ሕገ ወጥ የተባሉ አካላትን እውቅና የሰጠ ነው ፣ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያበረታታ እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው ይላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የካቢኔ አባላቶቻቸው በዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዳያስገቡ ማዘዛቸው "መንግሥት ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን ችላ ያለበት ነው" በማለት ቅዱስ ሲኖዶሱ ተችቷል።
ቤተ ክርስትያኗ በመንግሥት ይሁንታ "መፈንቅለ ሲኖዶስ እየተከናወነ እንዳለ እምነት የሚያሳድር" መሆኑን በመጥቀስ እርምት ጠይቃለች። ቤተክርስትያኗ ሕገወጥ ያለችው ቡድን አባላት ሕገ ወጥ ድርጊት እየፈፀሙ መሆኑንና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ መደረጋቸውን ገልጿለች።
"በሕገ ወጥ መንገድ ተሹመናል የሚሉት አካላት” በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወዳልተፈቀደላቸው የአገልግሎት ቦታዎች በመግባት በቤተክርስቲያኗ ላይ ሁከት እየተፈጠረ መሆኑን ለመረዳት ችለናል ያለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ይህ እንዲታረም ጠይቋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ኢዜማ "የሃይማኖት ተቋማት ላይ በማናቸውም ወገን የሚደረግ ጣልቃ ገብነት መዘዙ ብዙ ስለሆነ፤ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ" በማለት ሲያሳስብ "መንግሥት ሕገ ወጥነትን ከመደገፍ እና የቤተ ክርስትያን አባቶችን ከማዋከብ ይቆጠብ" ሲል እናት ፓርቲ ጠይቋል።
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ