የኢትዮጵያ ካፒታል ረቂቅ አዋጅ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 6 2013ማስታወቂያ
የኢዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ በተዘጋጀዉ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተለያዩ መሥሪያ ቤት ባለሙያዎችን ምክር ዛሬ አድምጧል። አርቃቂዎቹ እንደሚሉት አዋጁ ከዓለም አቀፍና ከሐገር ዉስጥ ተመሳሳይና ሌሎች ሕጎች ጋር ተጣጥሞ እንዲሠራ ታቅዶ የተረቀቀ ነዉ። ሐብታቸዉን በአክሲዎን ገበያ ላይ የሚያዉሉ ባለሀብቶችን መብትና ጥቅም ያስጠብቃል ፣ ቀልጣፋ የሠነድ መዋዕለ ንዋይ ሥርዓትንም ይፈጥራል ባዮችም ናቸዉ።አስተያየት የሰጡት የፋይናንስ ሙሕራን አዋጁ ከፀደቀ ጠንካራ የሒሳብ ያዢ ተቋም ፣ የፋይናንስ ጉዳይ ዘጋቢዎች መገናኛ ዘዴዎችና የዘርፉ ትንታኔ ሰጭዎች ተቋማዊ በሆነ መልኩ ሊደራጁ ይገባል ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ