1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ውኃ መማክርት ጥሪ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2016

የኢትዮጵያ መንግስት አገራዊ የአደጋ መከላከል ፖሊሲውን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን የተጠቆመው የማማክርቱ መግለጫ፣ በየደርጃው የማስፈጸም አቅምን ማጠናከርና ውጤታማ የተጠያቂነት ሥርዓት መዘጋት ያለውን ፋይዳ አስረድቷል። ድርቅን በብቃት ለመቆጣጠርና ረኃብን ለመከላከል፣ ሰላምና መረጋጋት ያለውን ጠቀሜታም አመልክቷል።

አንድ ወጣት ከሸበሌ ወንዝ ወኃ ሲቀዳ
አንድ ወጣት ከሸበሌ ወንዝ ወኃ ሲቀዳ ምስል AFP via Getty Images

የኢትዮጵያ ውኃ መማክርት ጥሪ

This browser does not support the audio element.


ኢትዮጵያ መንግስት የድርቅ አደጋን ወደ አገራዊ የጸጥታ ስጋት ደረጃ ከፍ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ውኃ መማክርት ጥሪ አቀረበ።

መማክርቱ ባወጣው ጋዜጣዊ  መግለጫ፣ድርቅን  በብቃት ለመቆጣጠርና ረሃብን ለመከላከል ስላምና መረጋጋት ወሳኝ መሆኑንም አመልክቷል።

የተደጋጋሚ ድርቅ ችግር

በኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ድርቅ፣ተያያዥ ረሃብና  የምግብ ዋስትና ችግሮች ታሪክ ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተመዘገበ መሆኑን ያመለክታል፣የኢትዮጵያ ውኃ ጉዳዮች መማክርት ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ። በዚህ በአሜሪካ በውኃ ጉዳዮች ላይ የሚያማክሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንን ያሰባሰበው መማክርቱ፣ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ 11 ያህል የድርቅ አደጋዎች መመዝገባቸውን ጠቅሷል።ባሕር እና ውቅያኖስ ላይ የተከሰው ሙቀት የጋበዘው ድርቅ

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ባደረገው የምግብ ዕርዳታ ፍላጎት ግምገማ፣ 15 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በያዝነው የጎርጎሮሳዊው 2024 ዓመት ረሃብ እንደሚገጥማቸው እና አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስቧል።  ከነዚህም መኻከል ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችና ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ወገኖች የአስቸኳይ የምግብ እጦት ችግር አለባቸው ብሏል።እንደ መግለጫው፣ ይህ ግምገማ  በኦሮሚያ፣ ዐማራና ትግራይ ክልሎች በጦርነት እና መጠን ሰፊ ግጭቶች ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን አያካትትም።

ከሁለት ዓመት በፊት በርካታ የቀንድ ከብቶች በድርቅ የሞቱበት የሀመር ወረዳምስል Hamar Woreda Government Communication Affairs Office

የድርቅ አደጋና የደህንነት ስጋት 

የኢትዮጵያ ውኃ ጉዳዮች መማክርት ፕሬዚዳንት አቶ መርስዔ እጅጉ፣በኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ እንዴት የፀጥታ ስጋት እንደሚሆን አስረድተዋል። የመጠጥ ውኃ ችግር በኢትዮጵያ
"በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ የወሎ ድርቅ ነው የአፄ ኃይለሥላሴን መንግስት ያናጋው፣ከዛም ከአንድ አስር አመት በኋላ ወደ 1977 ዓ.ም ላይ የደርግን ስርዓት ያናጋው ድርቅ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃም ስናየው፣ይህ የሕዝብ ደህንነት የሚባለው ለብዙ ዘመናት በሀገሮች ደረጃ ነበር የሚታየው። አንድ አገር ሌላውን ለማጥፋት ሲሞክር፣አንድ ሃገር ሌላውን ሲሰልል በ1970ዎቹ ላይ በራሱ  በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደረጃ የምግብ ዋስትና የሚባል መጣ።"የመማክርቱ የቦርድ አባል መቅደላዊት መሣይ በበኩላቸው ይህንን የፕሬዚዳንቱን ዐሳብ የሚያጠናክር አስተያየት ሰጥተውናል።

የረሃብ ተጽእኖ

"ድርቅ ለኢትዮጵያ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ድርቅ ሲከሰት ወደረሃብ መሸጋገር ባይኖርበትም በእኛ ሃገር ሁኔታ ሁልጊዜ ወደረሃብ ይሸጋገራል።እጅግ የብዙ ሰው ሕይወት ይጠፋል።ብዙ እንሰሳት ህይወት ይጠፋል።ብዙ ንብረት ይወድማል።ይህ ከሰውና ከእንሰሳት ህይወት መጥፋት ባሻገረር ብዙ ተጽዕኖ አለው።ሌላው ለኢኮኖሚያዊ ዕድገታችንም ቢሆን በጣም ተጽእኖ አለው።ድርቅ ወይም ረህሰሰይከሰታለች ብዙ እንስሳት ሂወት ይጠፋል ንብረት እንስሳት ህይወት መጥፋት ባሻገር ብዙ ለኢኮኖሚ እድገታችን ቢሆን ለብሄራዊ ደህንነትም ቢሆን በጣም ተጽእኖ አለው። ድርቅ ወይም ረሃብ መረጋጋት ሲከሰት በአገር ውስጥ የሚፈናቀሉ ሰዎች ይጨምራል  መረጋጋትን ያዛባል።"ድርቅ በአፋር ክልል ያስከተለው አደጋ

በአበርበገሌ ወረዳ እናትና ልጅ ውሀ ለመቅዳት እየሄዱምስል Million Haileselasie/DW

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት አገራዊ የአደጋ መከላከል ፖሊሲውን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን የተጠቆመው የማማክርቱ መግለጫ፣ በየደርጃው የማስፈጸም አቅምን ማጠናከርና ውጤታማ የተጠያቂነት ሥርዓት መዘጋት ያለውን ፋይዳ አስረድቷል።

ሰላምና መረጋጋት

ድርቅን በብቃት ለመቆጣጠርና ረኃብን ለመከላከል፣ ሰላምና መረጋጋት ያለውን ጠቀሜታም አመልክቷል። በፖለቲካ ፍላጎት ቁርጠኝነት፣በተሻሻለ ተቋማዊ አቅምና በተሻሻሉ ሳይንሳዊ መሳሪያዎች ድርቅን ወደ ረሃብ እንዳያመራ ማድረግ እንደሚቻል አቶ መርስዔ ጠቁመዋል።  "ድርቅ ቢኖርም በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ ህይወት መጥፋት፣ወደ እንሰሳት መሞት መሸጋገር የለበትም።"

የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ ምን እንደሚመስል ደግሞ የመማክርቱ የቦርድ አባል እንደሚከተለው አስረድተዋል።

"ድርቅ  ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ አይደለም ብዙ ቦታ ይከሰታል፡ ወደ ረሃብ የሚሸጋገረው ግን ቀድመን ስለማንጠነቀቅ ወይንም ፖሊሲዎቻችን ጠንካራ  ስላልሆኑ ነው የሚል ነው።ብለዋል።
 

ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW