1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ 

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 1 2010

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚስተናገዱበት አንድ የዲያስፖራ ኤጄንሲ የማቋቋም ሂደት መጀመሩ ተነገረ።  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  እንዳስረዱት፣ ተቋሙ የእነዚህን ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴ የሚያቀናብር እና የሚያቀናጅ ነው። ተጠሪነቱም ለፌዴራል መንግሥት ይሆናል።

Äthiopien Außenministerium Meles Alem
ምስል DW/Y. Egziabher

የዲያስፖራ ኤጄንሲ ሊቋቋም ነው ተባለ።

This browser does not support the audio element.

ጠ/ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በኤርትራ ያካሄዱት የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝትም በጋዜጣዊ መግለጫው የተነሳ ሌላ ጉዳይ ሲሆን፣ ቃል አቀባዩ የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ባካባቢው ሀገራት መካከል ትርጉም ያለው ልማት ለማምጣት ኤኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና የፀጥታ ትብብር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ለማጉላት ነበር ብለዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW