1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ቴክኒክአፍሪቃ

የኢትዮጵያ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መድረክ ልማት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 18 2013

ኢትዮጵያ በተለያዩ አገር በቀል ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጡ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መድረኮችን ለማበልጸግ እየሠራች መሆኑን የአገሪቱ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ (INSA) ዐስታወቀ። ኢትዮጵያ ላይ አድሏዊ አሠራርን ተከትለዋል የተባሉ ዓለማቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ኩባንያዎችን ለማነጋገር እቅድ መኖሩ ተገልጧል።

Symbolbild Apps Facebook und Google Anwendungen
ምስል picture-alliance/dpa/S. Stache

የራሳችን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መድረክ ያፈልጋል ተብሏል

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ በተለያዩ አገር በቀል ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጡ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መድረኮችን ለማበልጸግ እየሠራች መሆኑን የአገሪቱ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጄንሲ (INSA) ዐስታወቀ። የተቋመኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በተለይም ከለይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ቆይታ እንዳረጋገጡት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዓለማቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መድረኮችን የኢትዮጵያን አንድነት በሚያቀነቅኑ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ በግልጽ የሚታይ አድሏዊ አሠራር ዐሳይተዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ታበለጽጋለች የተባለው የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መድረኮች በተለያዩ አማራጮች መልእክት የሚያስተላልፉ የመረጃ ተግባቦት ቴክኖሎጂ ውጤቶች ሲሆኑ፤ መቼ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ግን ለጊዜው አልተገለጸም። ኢትዮጵያ ላይ አድሏዊ አሠራርን ተከትለዋል የተባሉ ዓለማቀፍ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ኩባንያዎችን ለማነጋገር እቅድ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን በትብብር በመርኅ ላይ ተመስርቶ አብሮ ለመሥረት እቅድ መኖሩም ተነግሯል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW