የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታና የመድረክ ወቀሳ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 7 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናቱ በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን በደልና የመብት ጥሰት አይከታተልም በማለት ዋነኛዉ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ወቀሰ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሰሞኑን ባሠራጨዉ ፅሑፍ እንዳለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚገደሉ፥ የሚታሰሩና እንዲሰደዱ የሚገደዱት ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።መድረክ እንደሚለዉ ለዜጎች ጥበቃ ማድረግ የሚገባዉ መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግ ቀርቶ በተገላቢጦሹ ባለሥልጣናቱ በተለይ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርሱትን ግፍና በደል እንኳን አላስቆመም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ የመድረክን ፕሬዝዳት ዶክተር ሞጋ ፍሪሳንና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሐላፊ አምባሳደር ጥሩነሕ ዜናን አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ