የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ጉባኤ መግለጫ
ዓርብ፣ ሰኔ 29 2004ማስታወቂያ
የሠብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሠመጉ) ከኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሠመኮ) ጋር ተፈራርሞት የነበረዉ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሥምምነት መፍረሱን አስታወቀ።ሠመጉ እንደሚለዉ ዉሉ የፈረሰዉ ኢሠመኮ ሥምምነቱን ገቢራዊ ለማድረግ ባለመፍቀዱ ነዉ።በሌላ በኩል በቅርቡ ባንጁል-ጋምቢያ ላይ ተሰይሞ የነበረዉ የአፍሪቃ የሠብአዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ይዞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ነዉ በማለት ያወጣዉን መግለጫ እንደሚደግፈዉ ሠመጉ አስታዉቋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሠ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ታደሠ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ